Author Archives: Central

በዘጠኝ ወራት ውስጥ የቆዳ ውጤቶችን ለውጭ ገበያ አቅርቦ 181 ነጥብ ሰባት ሚሊዮን ዶላር ዕቅድ ቢያዝም ማግኘት የተቻለው 99 ሚሊዮን ዶላር ብቻ ነው ተባለ።

በዘጠኝ ወራት ውስጥ የቆዳ ውጤቶችን ለውጭ ገበያ አቅርቦ 181 ነጥብ ሰባት ሚሊዮን ዶላር ዕቅድ ቢያዝም ማግኘት የተቻለው 99 ሚሊዮን ዶላር ብቻ ነው ተባለ። (ኢሳት ዜና ግንቦት 16 ቀን 2010 ዓ/ም) ይህም ከተያዘው ዕቅድ የተሳካው ግማሽ ያህሉ ብቻ መሆኑን የኢትዮጵያ ቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲት ዩት የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ ብርሃኑ ፍሪደሞ አመልክተዋል። ዕቅዱን ማሳካት ያልተቻለበት ዋነኛ ምክንያት የቆዳና ሌጦ ጥራት አለመሻሻሉ ...

Read More »

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከሰሜን ኮሪያው አቻቸው ጋር ለመገናኘት የያዙትን ፕሮግራም ሰረዙ።

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከሰሜን ኮሪያው አቻቸው ጋር ለመገናኘት የያዙትን ፕሮግራም ሰረዙ። (ኢሳት ዜና ግንቦት 16 ቀን 2010 ዓ/ም) በደቡብ ኮሪያ ሸምጋይነት ነበር የሁለቱ ባላንጣ ሀገር መሪዎች ዶናልድ ትራምፕና ኪም ዮንግ አን ለመጀመሪያ ጊዜ በሚቀጥለው ሰኔ ወር አጋማሽ ላይ እንደሚገናኙ ሲጠበቅ የቆዬ ቢሆንም፣ ፒዮንግያንግ አንዳንድ ተጨማሪ ቅድመ ሁኔታዎችን ለመቀበል ፈቃደኛ አለመሆኗ እና በቅርቡ ያወጣችው ቁጣ አዘል መግለጫ ዋሽንግተንን ቅውር ...

Read More »

በሰሜን ኮሪያ የኒዩክለር ሙከራ ጣቢያ ውስጥ ከባድ ፍንዳታ ተከሰተ

(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 16/2010) በሰሜን ኮሪያ የኒዩክለር ሙከራ ጣቢያ ውስጥ ከባድ ፍንዳታ መከሰቱ ተሰማ። ሰሜን ኮሪያ የሙከራ ጣቢያውን ከጎረቤቷ ደቡብ ኮሪያና ከአሜሪካ ጋር ያላትን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ለማጠናከር በሚል መዝጋቷን አስታውቃ ነበር። ከደቡብ ኮሪያና ከአሜሪካ ጋር የተጀመረውን ድርድር ተከትሎ ነው ከወራት በፊት  ሰሜን ኮሪያ ያላትን የኒኩለር ጦር መሳሪያ እንደምትቀንስ አስታውቃ የነበረው። በአሜሪካ በኩል ከኒዩክለር መሳሪያዎቼ ጋር በተያያዛ የአስገዳጅነት ሁኔታን ስለታዘብኩ ከአሜሪካው ፕሬዝዳንት ...

Read More »

በጨለማ እስር ቤት ላለፉት 24 ዓመታት የሚገኙት የሃይማኖት መምህር በአስቸኳይ እንዲፈቱ ተጠየቀ

(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 16/2010) በውጭ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኦሮቶዶክስ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ላለፉት 24 ዓመታት በጨለማ እስር ቤት የሚገኙት የሃይማኖት መምህር እንደስራቸው አግማሴ መኮንን በአስቸኳይ እንዲፈቱ ጠየቀ። ሲኖዶሱ ለኢሳት በላከው መግለጫ ላይ እንዳስታወቀው ከ24 ዓመት በፊት ተይዘው ጨለማ እስር ቤት ውስጥ ያለርህራሄ ታስረው የሚገኙት የሃይማኖቱ ሊቅ እንደስራቸው በህይወት መኖራቸው የታወቀው በቅርቡ ነው። እኚህ መምህር የቤተክርስቲያኒቱ ትልቅ ባለውለታ የሆኑና ያለጥፋታቸው በእስር የሚማቅቁ በመሆናቸው ...

Read More »

ሰማያዊ ፓርቲ ከተቋረጠው የድርድር ሂደት እንደገና እንዲመለስ ተጠየቀ

(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 16/2010) ሰማያዊ ፓርቲ ከተቋረጠው የድርድር ሂደት እንደገና እንዲመለስ ኢህአዴግ ጥሪ አቀረበ። የኢሕአዴግ ጽህፈት ቤት ሃላፊ ወይዘሮ ፈትለወርቅ ገብረእግዚአብሔር ለድርጅቱ በጻፉት ደብዳቤ ሰማያዊ ፓርቲ ወደ ድርድር ለመመለስ የመነሻ ሃሳብ እንዲያቀርብ ጠይቀዋል። ሰማያዊ ፓርቲ በሰጠው ምላሽ ግን ገለልተኛ አደራዳሪ በሌለበት ውይይት ለመጀመር እንደማይፈልግ ገልጿል። የኢሕአዴግ ምክር ቤት ጽሕፈት ቤት ሚያዚያ 30/2010 ለሰማያዊ ፓርቲ በጻፈው ደብዳቤ የፖለቲካ ድርጅቱ ወደ ድርድር ተመልሶ ...

Read More »

በቴፒ ከተማ በአማራ ተወላጆች ላይ ጥቃት እየተፈጸመ ነው ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 16/2010)በቤንች ማጂ ዞን ቴፒ ከተማ የህዝቡን ተቃውሞ አቅጣጫ ለማስቀየስ በአማራ ተወላጆች ላይ ጥቃት እየተፈጸመ ነው ተባለ። በዞኑና በዙሪያው ባሉ አካባቢዎች የመብት ጥያቄ በማንሳት የተጀመረው ተቃውሞ ሰሞኑን ተጠናክሮ በቀጠለበት ወቅት የአማራ ተወላጆችን ማጥቃትና ንብረታቸውን ማውደሙ ሆን ተብሎ በአገዛዙ የተፈጸመ ነው ሲሉ ኢሳት ያነጋገራቸው ነዋሪዎች ገልጸዋል። የህዝቡ ጥያቄ የነጻነትና የሀብት ተጠቃሚነት በመሆኑ ትግሉ እንደሚቀጥል የገለጹት ነዋሪዎች የእርስ በእርስ ግጭት እንዲሆን ...

Read More »

በዶሎ አዶ ከተማ 3 ሰዎች ተገደሉ

(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 16/2010) በሶማሌ ክልል በዶሎ አዶ ከተማ በተነሳው ህዝባዊ ተቃውሞ 3 ሰዎች መገደላቸው ተገለጸ። የክልሉ ልዩ ሃይል በወሰደው ርምጃ ከተገደሉት በተጨማሪ ሰባት ሰዎች ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰባቸው ለማወቅ ተችሏል። ሁለተኛ ወሩን እያገባደደ ያለው የሶማሌ ክልሉ ህዝባዊ ተቃውሞ ዛሬም በተለያዩ የክልሉ ከተሞች መቀጠሉን የደረሰን መረጃ አመልክቷል። በሌላ በኩልም በክልሉ በሚገኙ ሁለት ጎሳዎች መካከል ግጭት ተቀስቅሶ ሁለት ሰዎች መገደላቸው ታውቋል። በአብዲ ኢሌ ...

Read More »

የሃዋይ ጎሞራ የከርሰምድር ውሃ ማመንጫ ጣቢያ ላይ ጉዳት ሊያደርስ ይችላል ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 15/2010)በሃዋይ ከቀናት በፊት የተከሰተው ኪላዊያ እሳተ ጎሞራ ፍንዳታ በአካባቢው ባለ የከርሰምድር ውሃ ማመንጫ ጣቢያ ላይ ጉዳት ሊያደርስ ይችላል ተባለ። ከቀን ወደቀን እየተስፋፋ የመጣው ይህ እሳተጎምራ በከርሰ ምድር ሃይል ማመንጫው ላይ የሚደርስ ከሆነ ከባድ ፍንዳታ ከማስከተሉም በላይ አካባቢው በመርዛማ ጋዝ እንዲበከል ያደርገዋል የሚል ስጋትን ማጫሩ ተሰምቷል። ከዚህም ሌላ የእሳተ ጎመራው ፍንጣቂ ወደ ፓስፊክ ውቅያኖስ እየተወረወረ መሆኑ ደግሞ ሌላ አሳሳቢ ...

Read More »

የኦዴግ አመራሮች አዲስ አበባ ገቡ

(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 15/2010) የኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ግንባር /ኦዴግ/አመራሮች እነ አቶ ሌንጮ ለታ ዛሬ አዲስ አበባ ገቡ። ከመንግስት ጋር ድርድር መጀመሩን ከሳምንት በፊት በመግለጫ ያስታወቀውየኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ግንባር /ኦዴግ/አመራሮች በአቶ አባዱላ ገመዳ አቀባበል የተደረገላቸው ሲሆን፣ጉዟቸውን በተመለከተም ለጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥተዋል። በሃገር ቤት ፓርቲያቸውን በሕጋዊነት ለማስመዝገብ ወይንም ከሌሎች ጋር ተዋህዶ ለመስራት ሁኔታዎችን እንደሚያጤኑም ገልጸዋል። የትጥቅ ትግል ዲሞክራሲን አያመጣም ያሉት የኦዴግ ሊቀመንበር አቶ ሌንጮ ለታ ሌሎችም ...

Read More »

በደቡብ አፍሪካ ኢትዮጵያውያን ታላቅ የተቃውሞ ሰልፍ አካሄዱ

 (ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 15/ 2010)በደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ዛሬ በደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ፊትለፊት ታላቅ የተቃውሞ ሰልፍ አካሄዱ ። በደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያ ኤምባሲም ሰልፈኞቹን ላለማስተናገድ ቢሮውን ዝግ አድርጎ መዋሉም ታውቋል። ሰላማዊ ሰልፈኞቹ በቅርቡ ገዛህኝ ገብረመስቀል /ነብሮ/ በቅጥረኛ ነብሰ ገዳይ መገደሉን እንዲሁም ከዘረፋ ጋር በተያያዘ ሌሎች አስር ኢትዮጵያውያን  በደቡብ አፍሪካ መገዳላቸውን በመቃወም እንደሆነ ከአዘጋጆች ለማወቅ ተችሏል ። ለተቃውሞ ከተለያዩ የደቡብ አፍሪካ ከተሞች ...

Read More »