Author Archives: Central

በተለያዩ አካባቢዎች ግጭት ለማስነሳት ትንኮሳ የሚያደርጉ ሃይሎች እና ጠ/ሚኒስትሩን ለመግደል የሞከሩ ሃይሎች አንድ መሆናቸውን መንግስት አስታወቀ

በተለያዩ አካባቢዎች ግጭት ለማስነሳት ትንኮሳ የሚያደርጉ ሃይሎች እና ጠ/ሚኒስትሩን ለመግደል የሞከሩ ሃይሎች አንድ መሆናቸውን መንግስት አስታወቀ (ኢሳት ዜና ሰኔ 20 ቀን 2010 ዓ/ም) ሰኔ 16 ቀን 2010 ዓም በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ላይ በህዝቡ ላይ ጥቃት ለማድረስ የሞከሩ ሃይሎች በተለያዩ ቦታዎች የትንኮሳ ድርጊቶችን ሊፈጽሙ እንደሚችሉና ጥንቃቄ እንዲደረግ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት አስታውቋል። እነዚህ ሃይሎች በአገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች ትንኮሳዎችን ይፈጽማሉ የሚል ...

Read More »

በሆሳዕና ከተማ የድጋፍ ሰልፍ ተካሄደ። ባህር ዳር የድጋፍ ሰልፍ ለማድረግ ዝግጅት በሚደረግበት ወቅት በ3 አቅጣጫዎች ሊገቡ የነበሩ ቦንቦች ተይዘዋል። በሃረር ከተማ ደግሞ የድጋፍ ሰልፍ እንዳይካሄድ ክልከላ ተደርጓል።

በሆሳዕና ከተማ የድጋፍ ሰልፍ ተካሄደ። ባህር ዳር የድጋፍ ሰልፍ ለማድረግ ዝግጅት በሚደረግበት ወቅት በ3 አቅጣጫዎች ሊገቡ የነበሩ ቦንቦች ተይዘዋል። በሃረር ከተማ ደግሞ የድጋፍ ሰልፍ እንዳይካሄድ ክልከላ ተደርጓል። (ኢሳት ዜና ሰኔ 20 ቀን 2010 ዓ/ም) ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ የጀመሩትን የለውጥ እንቅስቃሴዎች በመደገፍ በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች ዛሬም በሆሳና ከተማ ቀጥሎ ውሎአል። የከተማዋ ነዋሪዎች በሆሳና ስታዲየም በነቂስ በመውጣት ለጠቅላይ ሚንስትሩ ያላቸውን አጋርነት ...

Read More »

የኤርትራ ልኡካን ቡድን አዲስ አበባ ገባ

የኤርትራ ልኡካን ቡድን አዲስ አበባ ገባ (ኢሳት ዜና ሰኔ 19 ቀን 2010 ዓ/ም) ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከኤርትራ የመጣውን ልኡካን ቡድን በቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ተገኝተው አቀባበል አድርገውለታል፡፡ የኤርትራው ፕሬዝዳንት አማካሪ እና የፖለቲካ ጉዳዮች ሃላፊ የማነ ገብረዓብ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ኦስማን ሳሌህና በአፍሪካ ህብረት የአገሪቱ አምባሳደር የሆኑት አርዓያ ደስታ ከልዑካን ቡድኑ አባላት መካከል ይገኙበታል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከኤርትራ ...

Read More »

በአሶሳ ብሄርን ማእከል ባደረገ ጥቃት 3 ሰዎች ተገደሉ

በአሶሳ ብሄርን ማእከል ባደረገ ጥቃት 3 ሰዎች ተገደሉ (ኢሳት ዜና ሰኔ 19 ቀን 2010 ዓ/ም) የአካባቢው ነዋሪዎች እንደገለጹት ከሳምንት በፊት በስልጣን ላይ የነበሩ የህወሃት አባላት በብሄር ብሄረሰቦች መካከል ግጭት እንዲፈጠር ለማድረግ በርታና ጉምዞች በአማራ እና ኦሮሞ ተወላጆች ላይ ጥቃት እንዲፈጸም አስደርገው 3 ሰዎች መሞታቸውንና ከ20 ያላነሱ ሰዎች ደግሞ ቆስለዋል። የህወሃት ሰዎች በአካባቢው እንደነበሩ እና ባምባሲና እና አሶሳ ዙሪያ እየዞሩ የበርታ ...

Read More »

የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ በፌዴሬሽን ምክር ቤት የተሰጠውን መልስ ተቃወመ

የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ በፌዴሬሽን ምክር ቤት የተሰጠውን መልስ ተቃወመ (ኢሳት ዜና ሰኔ 19 ቀን 2010 ዓ/ም) ኮሚቴው የፌዴሬሽን ምክር ቤት ሰኔ 4 ቀን 2010 ዓም የወልቃይት የአማራ ብሄርተኝነት አስመላሽ ኮሚቴ ያቀረበው የማንነት ይከበርልኝ ጥያቄ ህግን ተከትሎ ያልተካሄደ ነው በማለት ውድቅ ማድረጉን በጽኑ ተቃውሞአል። የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ በመግለጫው የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈጉባኤ ወይዘሮ ኬርያ ኢብራሒም ...

Read More »

የቱርኩ ፕሬዝዳንት በድጋሚ አሸነፉ

(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 18/2010) የቱርኩ ፕሬዝዳንት ሬስፕ ጣይብ ኤርዶጋን በድጋሚ ለፕሬዘዳንትነት መመረጣቸው ተሰማ። ኤርዶጋን 53 በመቶ ድምጽ በማግኘት ለቀጠዩ 5 አመታት ሀገሪቱን ለመምራት ያሸነፉ ሲሆን ተፎካካሪያቸው ሙሀራም ደግሞ 31 በመቶ የህዝብ ድምጽ ማግኘታቸውን ቢቢሲ ዘግቧል። ከተቃዋሚ ወገኖች ምርጫው ተጭበርብሯል የሚል እሳቤ መኖሩን ያሰፈረው የቢቢሲ ዘገባ ኤርዶጋን በስልጣን ዘመናቸው ውቅት 160 ሺ ሰዎችን ለእስር መዳረጋቸው ተገልጿል። ቭላድሜር ፑቲንን ጨምሮ የኢራኑ ፕሬዝዳንት ሃሳን ...

Read More »

በውጭ ምንዛሪ ተአቅቦ ላይ የተጠራው ዘመቻ ላልተወሰነ ጊዜ ተቋረጠ

(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 18/2010) በውጭ ምንዛሪ ተአቅቦ ላይ የተጠራውን ዘመቻ ላልተወሰነ ጊዜ ማቋረጡን ዓለም ዓቀፍ የኢትዮጵያውያን ግብረ ሃይል አስታወቀ። ግብረሃይሉ ለኢሳት በላከው መግለጫ እንደገለጸው በአሁኑ ወቅት የህወሃት አገዛዝ ተጽዕኖ እየተዳከመና የፖለቲካ አመራሩ በለውጥ ፈላጊዎች እጅ የወደቀበት ሁኔታን ከግምት በማስገባት የውጭ ምንዛሪ ተአቅቦው ዘመቻ ላልተወሰነ ጊዜ እንዲቋረጥ ተደርጓል። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በለውጥ ቀልባሾች ሊደርስባቸው የሚችለውን ኢኮኖሚያዊ አሻጥር ታሳቢ መደረጉን የገለጸው ዓለም ...

Read More »

የኢጋድ የፖለቲካ አማካሪ ኮለኔል ገብረእግዚአብሔር አለምሰገድ ከሃላፊነት ተነሱ

(ኢሳት ደሴ–ሰኔ 18/2010) የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት በየነ መንግስታት ድርጅት ኢጋድ የፖለቲካ አማካሪውን ማባረሩን አስታወቀ። የህወሀት ኮለኔል የሆኑት ገብረእግዚያብሄር አለምሰገድ ከዛሬ ጀምሮ ከኢጋድ ከፍተኛ የፖለቲካ አማካሪነት መነሳታቸውን የሚገልጽ ደብዳቤ እንደተሰጣቸው ለማወቅ ተችሏል። በኢጋድ ሴክቴሪያት አምባሳደር ማህቡብ ማሊም የተጻፈው ደብዳቤ ኮለኔል ገብረእግዚያብሄር አለምሰገድ ከዛሬ ሰኔ 18 ጀምሮ በእጃቸው የሚገኙ ንብረቶችን አስረክበው እንዲሰናበቱ የሚጠይቅ ነው። ኢጋድ ኮሎኔል ገብረእግዚአብሔርን በምን ምክንያት እንዳባረረ ግን አልገለጸም።

Read More »

በውጭ የሚገኘው ቅዱስ ሲኖዶስ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድን እደግፋቸዋለሁ አለ

(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 18/2010)በውጭ ሃገር የሚገኘው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድን እንደሚደግፍና ከጎናቸው እንደሚቆም ይፋ አደረገ። እንዲሁም በዋሽንግተን ዲሲ የሚገኘው የቀድሞ የኢትዮጵያ አየር ሃይል ማህበርም ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ጎን በመቆም አስፈላጊ የሆነውን ሁሉ ድጋፍ እንደሚያደርግም አስታውቋል። በብጹእ ወቅዱስ አቡነ መርቆሪዎስ ፓትሪያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘ ኢትዮጵያ የሚመራው ቅዱስ ሲኖዶስ ቅዳሜ ሰኔ 16/2010 ባወጣው መግለጫ ከጠቅላይ ...

Read More »

ኤፍ ቢ አይ በቦምብ ፍንዳታው ምርመራ ላይ እገዛ ያደርጋል ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 18/2010) በአዲስ አበባ ባለፈው ቅዳሜ  በመስቀል አደባባይ የፈነዳውን ቦምብ በተመለከተ የአሜሪካው የምርመራ ተቋም /ኤፍ ቢ አይ/ በምርመራው እገዛ እንደሚያደርግ ተገለጸ። የአሜሪካው የፌደራል የምርመራ ቢሮ ከሚያደርገው እገዛ በተጨማሪ ሃገራቸው ያልተገለጸ የውጭ ሃገር የምርመራ ባለሙያዎች ሒደቱን ለማፋጠን ኢትዮጵያ መግባታቸውን መንግስት አስታውቋል። የቅዳሜውን የቦምብ ጥቃት ተከትሎ የተቀነባበረ ጥቃት መፈጸሙን ያስታወቁት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ “ኢትዮጵያ ከጀመረችው የፍቅርና የይቅርታ መንገድ ሊገታት የሚችል ...

Read More »