Author Archives: Central

በመላ አገሪቱ የሚታየው የኑሮ ውድነት መክፋቱ ተነገረ::

ሐምሌ ፳፩ (ሀያ አንድ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም   ኢሳት ዜና:-  የኢትዮጵያ ስታትስቲክስ መስሪያ ቤት እና የገንዘብ ሚኒሰትሩ አቶ ሶፍያን አህመድ  የዋጋ ንረቱ እየወረደ ነው በማለት በተናገሩ ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ዋጋዎች እንደገና ወደ ላይ እየወጡ ነው። የእህል ዋጋ በከፍተና ፍጥነት እየጨመረ ሲሆን አንዳንድ የፍጆታ እቃዎችም ከገበያ እየጠፉ ነው። ዘይት ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ በዋና ከተማዋም ሆነ በክልል ከተሞች ጠፍቷል። ምግብ ...

Read More »

መንግስት በሙስሊሞች ላይ የሚሰራውን ድራማ በሲዳማ ለመፈጸም እየተዘጋጀ ነው ተባለ::

ሐምሌ ፳፩ (ሀያ አንድ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም   ኢሳት ዜና:- ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የድምጻችን ይሰማ ተቃውሞውን ለማኮላሸት መንግስት በክፍለሀገራት የሚገኙ ሙስሊም የሆኑና ሙስሊም ያልሆኑ ሰዎችን ከየቦታው በማሰባሰብ እንቅስቃሴውን እንዲያወግዙ በማድረግና በቴሌቪዥን ቀርጾ በማቅረብ ከፍተኛ የፕሮፓጋንዳ ስራ እየሰራ ሲሆን፣ ይህንኑ ስትራቴጂ በሲዳማ ላይ ለመድገም ዝግጅት ጀምሯል። በሲዳማ የተነሳው ተቃውሞ በተለያዩ ጊዜዎች እያገረሸ በንጹህን ዜጎች እና በፌደራል ፖሊስ አባላት ህይወት ላይ ጉዳት ...

Read More »

በአንዋር መስኪድ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ የሚሆን ህዝብ ትግላችን አይቀዘቅም አለ::

ሐምሌ ፳ (ሀያ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን በስፍራው ተገኝቶ እንደተመለከተው ዛሬ ለተቃውሞ የወጣው ሙስሊም ኢትዮጵያዊ እስከዛሬ ከተሳተፈው ሁሉ በቁጥር በእጅጉ የሚልቅ ነው። ዋና ዋና መሪዎቹ በማእከላዊ እስር ቤት በአሰቃቂ ድብደባ ምርመራ እየተካሄደባቸው መሆኑን የኢሳት እንዲሁም የአምነስቲ ኢንተርናሽናል መረጃዎች ይፋ ባደረጉ ማግስት፣ አንዳንዶች አንድ ሚሊዮን ሌሎች ከ700 ሺ እስከ 800 ሺ የሚገምቱት ህዝብ ተቃውሞውን በዝምታ፣ በጭብጨባና እጆቹን ...

Read More »

ሞያሌ ኣካባቢ በተነሳው ግጭት ከ20 በላይ ሰዎች ተገደሉ::

ሐምሌ ፳ (ሀያ)ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- ኢሳት የሞያሌ ነዋሪዎችን በስልክ አነጋግሮ ባጠናከረው መረጃ ከሶስት ቀናት በፊት በተነሳው ተቃውሞ ከ20 በላይ ሲቪሎችና 1 የፌደራል ፖሊስ ተገድለዋል። 7 ፖሊሶች ደግሞ በጽኑ ቆስለዋል። ግጭቱ የሶማሊ ብሄረሰብ ተወላጅ በሆኑ ገሪዎችና የኦሮሞ ተወላጅ በሆኑ ቦረናዎች መካከል የተፈጠረ ቢሆንም፣ የሁለቱም ክልል ፖሊሶች ጎራ ለይተው መታኮሳቸውን ነው ነዋሪዎች የሚገልጡት። ሞያሌ ከተማ በሁለት የክልል መንግስታት የምትተዳደር ከተማ ...

Read More »

የጤና ጥበቃ ሚኒስትሩ ዶክተር ቴዎድሮስ አድሀኖም፤ በአቡነ ጳውሎስ ተሾሙ።

ሐምሌ ፳ (ሀያ)ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- የአቡነ ጳውሎስ 20ኛ ዓመት በዓለ-ሲመት ሐምሌ 16 ቀን 2004 ዓ.ም ምሽት በሼራተን አዲስ ለሁለተኛ ጊዜ  በተከበረበት ጊዜ  ይፋ የሆነውንና በፓትርያርኩ ስም በ 200 ሚሊዮን ብር ወጪ ሊገነባ የታሰበውን ሆስፒታል በበላይነት እየተቆጣጠሩ እንዲያስፈፅሙ  ነው ሚኒስትር ቴዎድሮስ የተሾሙት። በዚሁ በሸራተን በተካሄደው የፓትርያርኩ  በዓለ-ሲመት ዝግጅት ላይ፤ የክብር እንግዳ የነበሩትን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩን አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝን እና  ...

Read More »

በመልጋ የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ በወንዶገነትም ተመሳሳይ ተቃውሞ ተነስቷል።

ሐምሌ ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- ከሶስት ቀናት በፊት በሲዳማ ዞን በመልጋ ወረዳ የተነሳው ተቃውሞ ወደ ወንዶገነትም ተዛምቶ፣ የባሻ ወረዳ ሊቀመንበር መገደሉንና የወረዳው መስተዳደር መኪና መቃጠሉን ዘጋቢያችን ገልጧል። በግጭቱም ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ፣ ነገር ግን በርካታ ቁጥር ያላቸው ፖሊሶች መቁሰላቸው ታውቋል። ሁለቱ ወረዳዎች ኩታገጠም ሲሆኑ፣ በመልጋ የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ የወረዳው ባለስልጣናት ህዝቡን ለማሳመን ወደ ታች ወርደው በሚነጋገሩበት ጊዜ ...

Read More »

አምነስቲ በሙስሊሞች ላይ አሰቃቂ ግፍ ተፈጽሟል አለ፡፡

ሐምሌ ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- አምነስቲ ኢንተርናሽናል ይህን ያስታወቀው “በሙስሊም ተቃዋሚዎች ላይ ከፍተኛ የሆነ የመብት ጥሰት ሳይፈጸም አልቀረም” በሚል ርእስ ባወጣው መግለጫ ላይ ነው። ድርጅቱ እንዳለው በእስር ላይ የሚገኙት ሙስሊም ተቃዋሚዎች፣ አሰቃቂ ድብደባ ( ቶርቸር) እንደተፈጸመባቸው የሚያሳዩ መረጃዎች አሉ ብሎአል። አንዳንድ እስረኞች ከቤተሰቦቻቸው እንዳይገኙ ተደርጎ ለብቻቸው መታሰራቸውን፣ በአንዳንዶች ላይም ጭካኔ የተሞላበት ድብደባ መፈጸሙን ገልጧል። ፖሊስ ተቃውሞውን ...

Read More »

ከሦስት ወረዳዎች 10 ሺህ ገበሬዎች ሊፈናቀሉ ነው የአካባቢው ባለስልጣን “የሚፈናቀል የለም” እያሉ ነው።

ሐምሌ ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- ከአርሲ ዞን ሦስት ወረዳዎች ብቻ ከ 10፣000 በላይ  ገበሬዎች “ቦታችሁ ለልማት ይፈለጋል” ተብለው ከይዞታቸው በግዳጅ ሊፈናቀሉ መሆናቸው ተሰማ። በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ከምዕራብ አርሲ ዞን ሶስት ወረዳዎች የተወከልን ነን የሚሉ ገበሬዎች ፦”ከሥራችንና ከመኖሪያችን እንድንነሳ  ማስጠንቀቂያ እየተሰጠን ስለሆነ፤ ፍትህ ይሰጠን” ሲሉ አቤት በማለት ላይ መሆናቸውን ፍኖተ ነፃነት ዘግቧል። ‹‹ከአያት ቅድመ አያቶቻችን ጀምሮ ተይዞ ...

Read More »

የአዲስአበባ አስተዳደር በቤት ልማት ስም የምርጫ ዘመቻ ጀመረ፡፡

ሐምሌ ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- የከተማ ልማትና ኮንስትራክሸን ሚኒስቴር ባለፈው ሳምንት ይፋ ያደረገው የ40 በ60 የቤት ልማት ፕሮጀክት በቀጣይ ዓመት ከሚካሄደው የአዲስአበባ አስተዳደርና የአካባቢ ምርጫዎች ጋር የተገናኘ መሆኑን ምንጮቻችን ጠቆሙ፡፡ ባለፈው በሒልተን ሆቴል የከተማ ልማት ሚኒስትሩ አቶ መኩሪያ ኃይሌ፣የአዲስአበባ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ኩማ ደመቅሳ በጋራ ያፋ ያደረጉት ፕሮግራም በአምስት ዓመታት ተከታታይ ጊዜያት ውስጥ የሚገነባውን ቤት ግምት ...

Read More »

ለፕሬስ ነፃነት ማንኛውንም መስዋትነት እንከፍላለን! ሲሉ የፍትህ ጋዜጠኞች ተናገሩ፡፡

ሐምሌ ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- የፍትህ ዋና አዘጋጅ የሆነው ተመስገን ደሳለኝ ዛሬ ባወጣው ጽሁፍ ” ነገም ፍትህ እንደወትሮዋ በመላ ኢትዮጵያ ጎዳናዎች አትነግስም፡፡ ምክንያቱ ደግሞ ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት ነው፡፡ በማለት ችግሩን እንደሚከተለው ዘርዝሯል። “ነገሩ እንዲህ ነው፡- ዛሬ ረፋዱ ላይ የፍትህ ጋዜጣ ሽያጭ ክፍል ሰራተኞች ማታ ወደማተሚያ ቤት ለምትገባው ጋዜጣችን ክፍያ ሊፈፅሙ ሄዱ፡፡ የማተሚያ ቤቱ ሃላፊ ደግሞ ...

Read More »