መስከረም ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በስዊዘርላንድ የሚገኘው ቢላል የሙስሊም ኢትዮጵያውያን ማህበር ከአለም አቀፉ የድምጻችን ይሰማ አስተባባሪ አካላት ጋር በጋራ በመሆን ባዘጋጀው በዚህ ደማቅ የተቃውሞ ሰልፍ ላይ ከተለያዩ የአውሮፓ ሃገራት የተውጣጡ የኮሙኒቲ ተወካዮች የተገኙበት ሲሆን ይዘውት የመጡትንም የአንድነትና የድጋፍ መልዕክት በሰልፉ ላይ ለተሳተፉ ታዲሚዎች አንብበዋል። የሰልፉ ዋና አስተባባሪ የሆኑት አቶ ኤልያስ ረሺዴ የዛሬ ሶስት ወር ገደማ ተመሳሳይ ሰልፍ ማድረጋቸውን ...
Read More »Author Archives: Central
ዲፕሎማቶች በዋናነት የሚገመገሙት በአመለካከት መሆኑ ታወቀ
(Sept. 14) ከአዲሱ 2005 ዓ.ም. ጀምሮ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መስሪያ ቤት ሰራተኞችና፤ ኢትዮጵያን ወክለው በውጭ አገራት የሚገኙ ዲፕሎማቶች ግምገማ፤ 60 ከመቶ አመለካከት 40 ከመቶ ደግሞ ሥራ ይሆናል ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚ/ር ምንጮቻችን ገለፁ። ውስጥ አዋቂ ምንጮቻችን እንደገለፁት ከሆነ ከያዝነው አዲስ አመት ጀምሮ በውጭ አገር የሚገኙ ዲፕሎማቶች የሚገመገሙት፤ ከምርጫ 97 በፊት እንደነበረው ከሲቪል ሰርቪስ መስሪያ ቤት በሚመጣ መገምገሚያ ቅጽ ሳይሆን፤ ምርጫ ...
Read More »በአቶ መለስ ዜናዊን የሐዘን መግለጫ ላይ በተተኮሰ ጥይት ሞትና ጉዳት ደረሰ
(Sept. 14) በአርማጭሆ አካባቢ በጠገዴ ወረዳ፤ ሰረቃ ከተማ፤ የአቶ መለስ ዜናዊን ሞት ተከትሎ በተዘጋጀ የሐዘን መግለጫ ዝግጅት ላይ በተተኮሰ ጥይት፤ አንድ አዋቂ መገደሉንና ሌላ ወጣት ደግሞ ቆስሎ ሆስፒታል መግባቱ ታወቀ። ኢሳት ከሥፍራው ያነጋገራቸው ሰው እንደገለጹት፤ ባለፈው ነሐሴ 21 ቀን በመንግሥት ባለሥልጣናት ትዕዛዝ በተዘጋጀው የሐዘን ዝግጅት ላይ፤ የአካባቢው ታጣቂዎች በሙሉ ለሐዘን መግለጫ የሚሆን ጥይት እንዲተኩሱ ታዘው በወቅቱ በተተኮሱ ጥይቶች፤ አንድ አዋቂ ወዲያውኑ ...
Read More »የኦጋዴን ተወላጆች መገደላቸውና ታፍነው መወሰዳቸው ታወቀ
(Sept 14) በኦጋዴን ብሄራዊ ነጻአውጪ ግንባር (ኦብነግ) እና በኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት መካከል የተካሄደው የመጀመሪያ ዙር የሰላም ድርድር እየተካሄደ በነበረበት ወቅት፤ ባለፈው አርብ 17 ንጹሀን የኦጋዴን ተወላጆች መገደላቸውና 14 ደግሞ ታፍነው መወሰዳቸው ታወቀ። አቶ ሀሰን አብዱላሂ፤ በኦብነግ የኢትዮጵያ ጉዳዮች ሀላፊ፤ ከኢሳት ጋር ባደረጉት አጭር ቃለምልልስ፤ ድርጊቱ መፈጸሙን አረጋግጠው፤ የአሁኑን ግድያ ለየት የሚያደርገው ግድያው የተፈጸመው የ7 አመት ህጻንን ጨምሮ፤ በመንግስት ቁጥጥር በእስርቤት ...
Read More »የሙስሊሞች የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ጉዳይ ለጥቅምት ተቀጠረ
(Sept. 14) በአስር ላይ የሚገኙት፤ የሙስሊሞች የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ጉዳይ፤ ለመጪው ጥቅምት 1 ቀን መቀጠሩን፤ የአዲስ አበባ ምንጮቻችን ገለጹ። በቀጠሯቸው መሰረት ከ28 ቀን በሁዋላ ትናንትና ሀሙስ መስከረም ሶስት ቀን በማረሚያ ቤት ሰራተኞች ወደፍርድ ቤት መቅረብ ያልቻሉት ተከሳሾች፤ ዛሬ አርብ በከፍጠኛ ጥበቃ ፍ/ቤት እንደቀረቡ ታውቋል። በዛሬው ችሎትም፤ አቃቤ ሕግ ምርመራዬን አልጨረስኩም ብሎ በጠየቀው መሰረት፤ ፍ/ቤቴ ለአቃቤ ሕግ ተጨማሪ 28 ቀን ...
Read More »የኢሕአዴግ ማዕከላዊ ምክር ቤት ሊቀመንበር እንደሚመርጥ አስታወቀ
(Sept. 14) የኢሕአዴግ ማዕከላዊ ምክርቤት፤ በዛሬ እና በነገው እለት በአዲስ አበባ ከተማ በሚያደርገው ስብሰባ የግንባሩን ሊቀመንበር እንደሚመርጥ አቶ በረከት ስምኦን አስታወቁ። ዛሬ ተጀምሮ በነገው ዕለት በሚጠናቀቀው የምክርቤቱ ጉባኤ የሚመረጠው የኢሕአዲግ ሊቀመንበር፤ በቀጥታ የሃገሪቱ ጠ/ሚ/ር እንዲሆን ኢሕአዴግ በዕጩነት እንደሚያቀርበው ታውቋል። የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስትር አቶ በረከት ሥምኦን፤ ለአዣን ፍራንስ ፕሬስ በሰጡት መግለጫ፤ የኢሕአዴግ ሊቀመንበር ሆኖ የሚመርጠው ሰው፤ በፓርላማው ጠ/ሚ/ር ሆኖ እንዲመረጥ ...
Read More »በሙስሊሞች ለተቃውሞ መሰባሰብ ምክንያት ፍርድ ቤት ችሎቱን በተነ
መስከረም ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ሀሙስ መስከረም 3 ቀን 2005 ዓም የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ አራዳ ምድብ ችሎት ከሰአት በሁዋላ በማእከላዊ እስር ቤት የሚገኙትን የኢትዮጵያን ሙስሊም ችግሮች መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላትና ሌሎች በእስር ላይ የሚገኙትን የተለያዩ መስኪዶች ኢማሞች እና የሙስሊሙ ማህበረሰብ አባላት ላይ ሊሰየም የነበረውን ዝግ ችሎት እጅግ በርካታ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን በጊዮርጊስ ዙሪያ በመሰባሰባቸው ህዝባዊ ቁጣ ይፈጥራል በሚል ስጋት ...
Read More »ክብርት አና ጎሜዝ አቶ መለስ የሞቱት በሐምሌ ወር እንደሆነ ተናገሩ
መስከረም ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ክብርት አና ማሪያ ጎሜዝ ይህን ያሉት፤ በኢትዮጵያ እየተፈጸመ ያለውን የሰብዓዊ መብት ጥሰት አስመልክተው ማክሰኞ ለአውሮፓ ፓርላማ ባደረጉት ንግግር ላይ ነው። አና ጎሜዝ በዚሁ ንግግራቸው ኢትዮጵያ ውስጥ በሚፈፀመው ከፍ ያለ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ዙሪያ -የአውሮፓ ህብረት ያሳየውን ቸልታ አጠንክረው ኮንነዋል። የአውሮፓ ህብረት ከፍተኛ እርዳታ ተቀባይ እና ከአፍሪካ በህዝብ ብዛቷ ሁለተኛ በሆነችው ኢትዮጵያ፤ ባለፈው ሐምሌ ...
Read More »ከኢህአዴግ መሪዎች የሚጠበቀው፤ ላልተመለሱ ጥያቄዎች መልስ መስጠት ነው ሲሉ አቶ ስዬ አብርሀ ተናገሩ
መስከረም ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-አቶ ስዬ ይህን ያሉት መድረክ በሲያትል ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ጋር ባደረገው ስብሰባ ላይ ባደረጉት ንግግር ነው። <ነፍሱን ይማረውና ከ እንግዲህ አቶ መለስ አርፏል፤አልፏል> ያሉት አቶ ስዬ፤ ከ እንግዲህ የሚቋቋመው መንግስት የ አቶ ሀይለማርያም ወይም ከሌሎቹ የ አንዱ ይሆናል እንጂ የመለስ አይሆንም>ብለዋል። <ተወደደም ተጠላም የምናውቀው ኢህአዴግ ከ እንግዲህ አይኖርም>ሲሉም አቶ ስዬ አክለዋል። <የ ኢትዮጵያ ሕዝብ ...
Read More »አፍሪካ 4 ነጥብ 5 በመቶ እድገት ታስመዘግባለች ተባለ
መስከረም ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በኢሲኤ የስብሰባ አዳራሽ የቀረበው የተመድ ሪፖርት እንደሚያሳዬው በተያዘው አመት መጨረሻ በአፍሪካ 4 ነጥብ 5 በመቶ እድገት ሊገኝ ይችላል። ከሁለት አመት በፊት በአህጉሪቱ የታየው የ5 በመቶ እድገት አምና በአለም ላይ ከተፈጠረው የኢኮኖሚ ቀውስንና ከአረቡ አብዮት ጋር ተያይዞ በዚህ አመት ሊደገም አለመቻሉ በሪፖርቱ ተመልክቷል። በአህጉሪቱ እየጨመረ የመጣው ስራ አጥነት የአገራትን ሰላምና ደህንነት አደጋ ውስጥ እንደጣለው ...
Read More »