ዛሬ በአንድነት ፓርቲ ላይ የተላለፈው ውሳኔ የፍትህ ስርአቱን ብሉሽነት የሚያሳይ ነው ተባለ

ሐምሌ ፴ (ሰላሳ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-በእነ አንዷለም አራጌ የክስ መዝገብ የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 3ኛ ወንጀል ችሎት ያሳለፈውን የቅጣት ውሳኔ ተከትሎ አንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ ፓርቲ ባወጣቸው መግለጫዎች ላይ ነው ፍርድ ቤቱ ትእዛዙን የሰጠው።

አንድነት ፓርቲ ሰኔ 24 እና ሀምሌ 8 በእነአቶ አንዱአለም አራጌ ላይ የተላለፈውን ውሳኔ በጽኑ ማው  ገዙ ይታወቃል።

የፓርቲው መግለጫ የፍርድ ቤቱን ነጻነት የሚጋፉ ብሎም አደጋ ላይ የሚጥሉ በመሆናቸው የፓርቲውን ዋና ጸሀፊ አቶ አስራት ጣሴን አስጠርቶ በመጠየቅ፤ መግለጫዎቹ የሀረግ ችግር እንዳለባቸው እንቀበላለን፤ ከሌሎች የፓርቲው አመራሮች ጋር ተነጋግረን ውሳኔ እናስተላልፋለን በማለት መናገራቸውን ገልጿል።

የፓርቲው ፕሬዝዳንት ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ፣ ምክትላቸው አቶ ግርማ ሰይፉና ዋና ጸሀፊው በተገኙበት እሎት፣ ፍርድ ቤቱ ፓርቲው የፈጸመው ጥፋት ከባድ ቢሆንም፣ ድርጅቱ ለመድለ ፓርቲ ስርአት ግንባታ የሚያደርገው አስተዋጽኦ ከፍተኛ በመሆኑ በተግጻጽ እንዲታለፍ ወስኗል።

ውሳኔውን በተመለከተ የአንድነት ፓርቲ ዋና ጸሀፊ የሆኑት አቶ አስራት ለኢሳት እንደገለጡት፣ በአንድነት ላይ የተወሰነው ውሳኔ የፍትህ ስርአቱ መበላሸቱን የሚያሳይና ይበልጥ የሚያጋልጣቸው ነው ብለዋል።

ከአቶ አስራት ጣሴ ጋር የተደረገው አጭር ቃለምልልስ ከዜናው በማስከተል ይቀርባል::

_____________________________________________________________________________________________

ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.

ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide