ግንቦት 7 የፍትህ የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ አመታዊ ስብሰባውን በተሳካ ሁኔታ መካሄዱን ገለጸ።

ሐምሌ ፳፮ (ሀያ ስድስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:- ግንቦት 7 የፍትህ የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ከሃምሌ 22 እስከ ሃምሌ 24 ቀን 2004 ዓም ድርስ ባካሄደው የንቅናቄው አመታዊ ስብሰባ በአገራችን ወቅታዊ ሁኔታ ላይ በስፋት በመነጋገር በአስቸኳይ ሊተገበሩ ይገባቸዋል ባላቸው የተለያዩ ጉዳዮች ላይ ውሳኔ ማስተላለፉን የንቅናቄው የህዝብ ግንኙነት ክፍል ለኢሳት በላከው መግለጫ አስታውቋል።

የመለስ ዜናዊ አገዛዝ ላለፉት 21 አመታት የተገበራቸው የዘረኝነት ፖሊሲዎች በህዝባችን መሃል የፈጠራቸው ብሶትና ምሬቶች ፈንድተው የአገዛዙን ዕድሜ ለማሳጠር ለሚደረገው የነጻነት ትግል ምቹ ሁኔታዎች በፈጠሩበት በአሁኑ ሰዓት የተካሄደው ይህ የግንቦት 7 አመታዊ ስብሰባ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ ከተነጋገረባቸውና ውሳኔ ካሳለፈባቸው ጉዳዮች አንዱ ከአገዛዙ  መደምሰስ በኋላ ሊፈጠር ስለሚገባው የሽግግር ወቅትና በአገራችን ሊመሰረት ስለሚገባው የዲሞክራሲ ሥርዓት መሆኑን አስታውቋል።

ንቅናቄው በዚህ አመታዊ ስብሰባው የወቅቱ የአገራችን ሁኔታ የፈጠረውን ስጋት ለማስወገድ የሚጠበቅበትን ሃላፊነት ሁሉ በቁርጠኝነት ለመወጣት ዝግጁ እንደሆነና  በምድር ላይ የሚያካሂደውን ትግል ከሌሎች ተመሳሳይ የትግል ስልት ከሚከተሉ ድርጅቶች ጋር በመሆን ለማፋጠን እንደወሰነ ገልጧል።

___________________________________________________________________________________________________________________________________________________

ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.

ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide