ሐምሌ ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-በኢትዮጵያ ባለፈው እሁድ ስድስት የሳኡዲ ዜጎች በሽብርተኝነት ተጠርጥረው መታሰራቸው ተዘገበ።
“ ሳዑዲ ጋዜጣ” እንደዘገበው የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ስድስት የ ሳዑዲ ዜጎችን ያሰሩት፦” ሽብርተኝነትን በገንዘብ ትደግፋላችሁ” በማለት ነው።
ጋዜጣው እንዳለው የታሰሩት ስድስቱ የሳዑዲት ዓረቢያ ዜጎች በተለያዩ ማህበራዊ ጉዳዮች ሙስሊሞች ያሉባቸውን ችግር ለመቅረፍ በአዲስ አበባ እየተንቀሳቀሱ የነበሩ በጎ አድ ራጊዎች ነበሩ።
በ አዲስ አበባ የሳኡዲ ኤምባሲ አንድ ከፍተኛ ባለስልጣን ፦” አል ዋታን አረቢክ” ለተባለ የሳዑዲ ዕለታዊ ጋዜጣ በስልክ እንደተናገሩት፤ ስድስቱ የ ሳዑዲ ዜጎች የታሰሩት ለችግረኞች የሚሆን እርዳታ በሚያከፋፍሉበት ጊዜ ነው።
በአሁኑ ጊዜ በኤምባሲው አማካይነት ለታሳሪዎቹ ጠበቃ መቆሙንና የሚፈቱበትን ሁኔታ ለማመቻቸት ጥረት እየተደረገ መሆኑን ጋዜጣው አመልክቷል።
___________________________________________________________________________________________________________________________________________________
ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.
ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide