በዋልድባ ገዳም መነኮሳት እየታደኑ ነው

ሰኔ ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-አንድ ስማቸው እንዳይገለጥ የፈለጉ የገዳሙ መነኩሴ ለኢሳት እንደተናገሩት መንግስት የህዝብን ተቃውሞ ጆሮ ዳባ ልበስ በማለት የገዳሙን አካባቢ ማረስ መጀመሩን የተቃወሙ 5 መነኮሳት በፌደራል ፖሊስ ተይዘው ታስረዋል።

3ቱ መነኮሳት ማይጸብሪ ወይም አድርቃይ አካባቢ ተወስደው መታሰራቸውን የተናገሩት አባት፣ ሁለቱ ግን አድርቃይ ተወስደው መታሰራቸውን እንደሚያውቁ ተናግረዋል።

ጨመው በር እና አጠላ የሚባሉ አካባቢዎች የሚኖሩ ነዋሪዎች የመነኮሳቱን መታሰር በማስመልከት የተቃውሞ ሰልፍ ቢያደርጉም በፖሊስ እንዲበተን ተደርጎአል።

የመንግስት ባለስልጣናት ህብረተሰቡ የእርሻ ስራው በገዳሙ ላይ ምንም ችግር እንደማያመጣ ተረድቶ ተቃውሞውን አቁሟል በማለት እየተናገሩ ነው ፣ ይህ እውነት ነው ወይ ተብሎ ለቀረበላቸው፣ መነኩሴው በፍጹም ብለዋል::

መንግስት የእርሻ ስራው ገዳሙን አይነካም በማለት የሚያካሂደው ቅስቀሳ የተሳሳተና ህዝቡን ለማደናገር ተብሎ የሚነገር መሆኑን መነኩሴው ይገልጣሉ::

የዋልድባ ገዳም መነኮሳት ለህይወታቸው ዋስትና እያጡ መመምጣታቸውንም መነኩሴው ተናግረዋል።

___________________________________________________________________________________________________________________________________________________

ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.

ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide