በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሠራተኛው ላይ የ 7 አመት ከ 8 ወራት እስራት ተበየነ

ሰኔ ፲፮ (አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-ፍርድ ቤቱ አብዱራሂም ሺሁ ሀሰን በተሰኘው የመንግስታቱ ድርጅት የሴኩሪቲ ኦፊሰር ላይ ይህን ውሳኔ ያሳለፈው፦ “ለኦጋዴ ብሄራዊ ነፃነት ግንባር መረጃዎችን  አስተላልፏል” በማለት በ ፌዴራል አቃቤ ህግ  በተመሰረተበት ክስ ጥፋተኛ ሆኖ በመገኘቱ እንደሆነ ገልጿል።

አብዱራሂም  የሽብርተኝነት ክስ ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ፤  ዓለማቀፍ የሰብዓዊ መብት ተቋማት፦  የኢትዮጵያ መንግስት  ተዓማኒነት የሌለውን ክሱን ውድቅ በማድረግ የመንግስታቱ ድርጅት የደህንነት ሠራተኛን ይፈታ ዘንድ ተደጋጋሚ ጥያቄ ማቅረባቸው ይታወሳል።

እንደ ብሉም በርግ ዘገባ፤በመንግስታቱ ድርጅት ሠራተኛ ላይ የ እስር ውሳኔውን ያስተላለፉት፤ ዻኛ ሙሉጌታ ኪዳኔ ናቸው።

በተመሣሳይ ማርቲን ሽብዬ እና ጆሀን ፔርሰን የተባሉት ሁለት ስዊድናውያን ጋዜጠኞች ከኦጋዴ ነፃነት ግንባር ጋር ግንኙነት አላችሁ ተብለው  እያንዳንዳቸው  የ11 ዓመት እስራት እንደተበየነባቸው መዘገቡ ይታወሳል።

ጉዳዩን እያስቻለ ያለው ፍርድ ቤት የተመሰረተባቸውን የፈጠራ ክስ የተቀበለው ከመሆኑ አንፃር ፤ እነ እስክንድር የሞት ወይም የእድሜ ልክ እስራት እንደበየንባቸው ይጠበቃል።

ጉዳዩን በቅርበት እየተከታተሉ ያሉ ወገኖች፤እነ እስክንድር “ክሱን በሽምግልና ለመጨረስ” በሚል ሰበብ ይቅርታ ይጠይቁ ዘንድ እየተደረገ ላለው የውስጥ ለውስጥ ማባበል ምንም ዓይነት ቀዳዳ ሊከፍቱ ባለመቻላቸው ፤ገዥው ፓርቲ ከፍ ያለ የፍርድ ውሳኔ እንዲተላለፍ በማድረግ ከአቋማቸው ለማንሸራተት ሙከራ እንደሚያደርግ ይጠበቃል ይላሉ።

___________________________________________________________________________________________________________________________________________________

ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.

ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide