ጋናውያን በመጪው ምርጫ ጨዋነት፣ ትእግስትና ብስለት እንዲያሳዩ በጋና የኢትዮጵያ አምባሳደር አሳሰቡ

ግንቦት ፳፫ (ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-አምባሳደር ጊፍቲ አባስያ ይህን የተናገሩት የግንቦት20ን በአል በኢትዮጵያ ኢምባሲ ተገኝነተው ባከበሩበት ወቅት ነው። አምባሳደሩዋ በግሌ ” የጋና ህዝብ በምርጫ 2012 ከዚህ በፊት ያሳየውን ጨዋነት፣ ብስለትና ታጋሽነት እንዶደግም “ጥሪ አቀርባለሁ ብለዋል።

ኢማኑኤል ዶግቤቪ እንደዘገበው አምባሳደሩዋ በጋና እና በኢትዮጵያ መካከል ያለው የኢኮኖሚ ግንኙነት የተጠናከረ አለመሆኑንም ተናግረዋል።

ጋና በአፍሪካ ውስጥ ዲሞክራሲያዊ ምርጫ ካደረጉ በጣት ከሚቆጠሩ አገሮች መካከል ትጠቀሳለች። በመልካም አስተዳደር እና በኢኮኖሚ እድገትም ተጠቃሽ አገር ናት። ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ በጋና ተገኝተው ለአፍሪካዊያን መልእክቶችን ሲያስተላልፉ ጋና የአፍሪካ የዲሞክራሲ ምሳሌ እንደምትሆን ተናግረው ነበር። በአንጻሩ ኢትዮጵያ የጭቆናና የምርጫ ማጭበርበር ተምሳሌት ተደርጋ በአለማቀፍ የመገናኛ ብዙሀን ትሳላለች። በ2002 ምርጫ የመለስ መንግስት 99 ነጥብ 6 በመቶ ድምጽ በማሸነፍ የአፍሪካን የዲሞክራሲ ተስፋ እንዳጨለመ በተደጋጋሚ ይዘገባል።

አምባሳደር ጊፍቲ ለጋና ህዝብ ያስተላለፉት መልእክት አስገራሚነቱ የሚነሳው ከዚህ ነው ይላሉ አስተያየት ሰጪዎች። ኢትዮጵያ ጋናን ስለ ዲሞክራሲያዊ ምርጫ ለመምከር የሞራል ብቃት የላትም ብቻ ሳይሆን አስቂኝና ፌዝ ነው እንደ አስተያየት ሰጪዎች።

___________________________________________________________________________________________________________________________________________________

ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.

ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide