ኢትዮጵያውያን ግንቦት20 ሀዘን ይዞልን የመጣ በመሆኑ በሀዘን ነው የምናከብረው ይላሉ

ግንቦት ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-ኢህአዴግ ወደ ስልጣን የመጣበትን 21ኛ አመት እያከበረ ባለበት ወቅት በተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን አነጋገረናል። አንድ ስሟ እንዳይገለጥ የፈለገች በቤንሻንጉል አካባቢ የምትኖር ኢትዮጵያዊት ግንቦት20 ለኢትዮጵያ ሀዘንን ፣ ውድቀትና ጥፋትን ይዞ የመጣ በመሆኑ ቀኑን በሀዘን እንደምታከብረው ገልጻለች።

ወጣቷ ግንቦት 20 ለኢትዮጵያ የኢኮኖሚና የፖለቲካ ድል ይዞ መመምጣቱ ይነገራል ምን አስተያየት አለሽ ተብላ ለተጠየቀችው   ሰትመልስ በአገሪቱ  ረሀብ እየከፋ መምጣቱ እና በዚህም የተነሳ ዘመዶቿን እስከማጣት በመድረሷ ግንቦት20 የኢኮኖሚ እድገት አስገኝቷል የሚለው ባዶ ፕሮፓጋንዳ መሆኑን ገልጣለች::

ሌላ ስማቸው እንዳይገለጥ የፈለጉ በኦሮሚያ አካባቢ የሚኖሩ ሰው በበኩላቸው ገዢው ፓርቲ የህዝብን አደራ የበላ በመሆኑ በሀዘን እንደሚያከብሩት ገልጠዋል።  አርባ ምንጭ ኒውስ::

ኢህአዴግ የኢኮኖሚ እድገት ማግኘቱ የግንቦት 20 ስኬት ውጤት ነው ይላል እርስዎስ ምን ይላሉ ተብለው ለተጠየቁት ግለሰቡ ሲመልሱ ፣ አሁን ያለው እድገት ሳይሆን ውድቀት ነው የሚል መልስ ሰጥተዋል ።

በደቡብ ክልል የሚገኙ  አንድ ኢትዮጵያ ደግሞ ግንቦት 20 ለገዢው ፓርቲ ፈንጠዝያን ይዞ ቢመጣም ለኢትዮጵያ ህዝብ ችጋርን፣ የሰብአዊ መብት ጥሰትን ይዞ የመጣበት በመሆኑ አንገታችንን ደፍተን ነው ይላሉ ::

ገዢው ፓርቲ በብሄር ብሄረሰቦች ፖሊሲው ህዝቡ እርስ በርስ እንዲተላለቅ ሁኔታዎችን ማመቻቸቱንም እኝሁ ተወላጅ ይገልጣሉ፡፡

ገዢው ፓርቲ የኢኮኖሚ እድገት አምጥቻለው የሚለው ተቀባይነት የሌለው ነገር መሆኑን ግለሰቡ ይከራከራሉ።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ገዢው ፓርቲ የዘንድሮው በአል በእየመስሪያ ቤቱ የስብሰባ አዳራሾች  እንዲካሄድ አድርጓል። ኢህአዴግ ቅዳሜ እና እሁድ ከሴቶች ዛሬ ደግሞ  ከወጣቶችን ጋር በመሆን በአሉን አክብሯል ። የኢሳት የመረጃ ምንጮች እንደገለጡት ለእያንዳንዱ ተሰብሳቢ ኢህአዴግ 20 ብር አበል ከፍሎአል።

___________________________________________________________________________________________________________________________________________________

ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.

ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide