ሚያዚያ ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-በዛሬው እለት ቁጥራቸው በርካታ የሆኑ በስዊዘርላንድ እና ኣካባቢዋ ነዋሪ የሆኑ ኢትዮጵያውያን ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ ኣካሄዱሰልፉ የተዘጋጀው ኢህአዴግ :- · ዋልድባ ገዳምን ጨምሮ በሁሉም የእምነት ተቋማት ላይ እያካሄደ ያለውን ጣልቃ ገብነት በመቃወም ፣ · የሽብርተኝነት ታርጋ እየለጠፈ በንጹሐን ዜጎች ላይ የሚያካሄደውን አፈናና የመብት ረገጣ በመቃወም ፣ · የዜጎችን ከቦታ ቦታ የመንቀሳቀስ መብት በመገደብ በሕዝባችን ላይ እየደረሰ ያለውን መፈናቀል በመቃወም ፣ · በኢንቨስትመንት ስም በውጭ ባለሀብቶች አማካይነት እየተካሄደ ያለውን የመሬት ቅርምትና የዜጎች ከቀያቸው መፈናቀል በመቃወም ፣ · መምህራን ያቀረቡትን የመብት ጥያቄ በአግባቡ ከመመለስ ይልቅ ጥያቄውን ለማዳፈን እየሄደበት ያለውን መንገድ በመቃወም ፣ · በአጠቃላይ ሐገራችን ኢትዮጵያ አሁን ለምትገኝበት አስከፊና አሳዛኝ ሁኔታ የዳረጋትን ብልሹ፣ ጨቛኝና አምባገነን የአገዛዝ ስርዓት በመቃወም ነው ።
በስዊዘርላንድ ነዋሪ የሆኑ የተለያዩ የፖለቲካ ድርጅት ደጋፊዎች፣የሲቪክ ማህበረሰብ ኣባላት፣የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ፣ የእስልምና እና የተለያዩ የእምነት ድርጅት ተወካዮች እና ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያውያኖች ናቸው ሰልፈኞቹ ። በተለይም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ወያኔ በእምነት ተቋማት ላይ የከፈተውን የጥፋት እና የመከፋፈል ርምጃ በፅኑ ተቃውመዋል :: ኣስተባባሪዎች የተቃውሞ ዳቤያቸውን
ለተባበሩት መንግስታት የሰብኣዊ መብት ኮሚሽን ኮሚሽነር ፣ ለተባበሩት መንግስታት የትምህርት የሳይንስና ባህል ድርጅት ፣ለኣለም ኣብያተ ክርስቲያን ጽ /ቤት ፣ ለኣለማቀፉ የቀይ መስቀልና ቀይ ጨረቃ ማህበር እንዲሁም ለተለያዩ ኣለም ኣቀፍ ተቋማት ኣስገብተዋል:: ዘገባው የጴጥሮስ አሸናፊ ነው
___________________________________________________________________________________________________________________________________________________
ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.
ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide