የቦብ ማሪሊንን የህይወት ታሪክ የሚዘክር ዘጋቢ ፊልም ተሰራ

ሚያዚያ ፲፫ (አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-በኦስካር ተሸላሚው ኬቪን ማክዶናልድ የተሰራው ፊልም የቦብ ማርሊን ህይወት ከሚገልጹት ፊልሞች ሁሉ የተሻለ ነው ተብሎአል።

ፊልሙ ቦብ ማርሊንን ብሄራዊ ጀግና ለማድረግ ለተጀመረው እንቅስቃሴ እገዛ እንደሚያደርግ ታውቋል።

በኪንግስተን ፓርክ በተደረገው የመክፈቻ ዝግጅት በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ጃማይካዊያን ተሳትፈዋል። በዝግጀቱ እለት ለመንግስቱ ባለስልጣናት መረማመጃ ተብሎ የተነጠፈው ቀይ ቢጫ እና አረንጓዴ ባንዲራ ፣ በተመልካቹ ተቃውሞ እንዲነሳ ተደርጓል። እነዚህ ሶስቱ ቀለማት ለጃማይካዊያን የተቀደሱ ቀለማት ናቸው።

በለጋ እድሜው የተቀጨው የሬጌ ሙዚቃ ንጉሱ ቦብ ማርሊን ፣ ጌት አፕ ስታንዳፕ፣ ኖ ውመን ኖ ክራይ በመሳሰሉት ውብ ዘፈኖቹ ይታወቃል።

___________________________________________________________________________________________________________________________________________________

ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.

ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide