መጋቢት ፳፩ (ሃያ አንድ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-የፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት 3ኛ ወንጀል ችሎት ውሳኔውን ያሳለፈው በ6 የአርበኞች ግንባር አባላት ላይ ሲሆን፣ በአንደኛ ተከሳሽ ሲሳይ ብርሌ የ13 አመት ጽኑ እስራት፣ ከ2ኛ እስከ 6ኛ በተዘረዘሩት ተከሳሾች ቢራራ አለሙ፣ ማንደፍሮ አካልነው፣ ዘመድየ አገዘ፣ መሰለ ድንቁና ቴዎድሮስ አያሌው ላይ ደግሞ የ10 አመት እስራት ፈርዷል።
በእስር ላይ የሚገኙት ተከሳሾች የአርበኞች ግንባር አባላት በመሆን ኤርትራ ሄደው ስልጠና በመውሰድ እና በገንዘብ ዝውውር ተከሰዋል።
የኢትዮጵያ መንግስት ለስልጣኑ ስጋት ይሆናሉ ብሎ የሚጠረጥራቸውን ሁሉ በሽብርተኝነት እየከሰሰ በእስር እንደሚያሰቃይ ይታወቃል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ኢንተርናሽና ፕሬስ ኢንስቲትዩት እስክንድር ነጋና ሌሎች በሽብርተኝነት ተጠርጥረው የታሰሩ ጋዜጠኞች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ ጠይቋል። የፕሬስ ተቋሙ ባወጣው መግለጫ እነእስክንድር ነጋ ሀሳባቸውን በነጻነት በመግለጻቸው በሽብርተኝነት መከሰሳቸው ፣ እውነተኛ አሸባሪዎችን ለመታገል የሚደረገውን ጥረት የሚያበላሽ ይሆናል።
የተመድ ዋና ጸሀፊ የሆኑት ባንኪሙን በእስር ላይ የሚገኙት ጋዜጠኞእ እንዲፈቱ ጫና እንዲያደርጉ መጠቁን ኢንስቲቲዩቱ አስታውሷል።
___________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________
ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.
ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide