መጋቢት 7 ቀን 2004 ዓ/ ም
ኢሳት ዜና:-የህዝቅተኛ የኦሞ ሸለቆ አካባቢ ነዋሪዎችን ከቦታቸው በማንሳት በቦታው ላይ የሸንኮራ ገዳ ተክል ለመትከል መታቀዱን በድብቅ የወጣው ሪፖርት ያመለክታል።
ሰርቫይቫል ኢንተርናሽናል በደረሰው መረጃ የሙርሲ፣ የቦዲና የኩዌጎ ነዋሪዎችን በቦዲ ለማስፈር ዘግጅቶች እየተካሄዱ ነው።
በአካባቢው ከፍተኛ የሆነ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት እየተካሄ መሆኑን ተገልጧል። አንድ የሙርሲ ተወላጅ ” መንግስት መሬቴን ስለወሰደው ሞትን እየተጠባበኩ ነው። ” ብሎአል።
ሌላ የቦዲ ተወላጅ ደግሞ መንግስት እየዋሸን ነው። መንግስት ወደ ሌላ ቦታ ከሄድን የምንበላውንና የምንጠጣውን እሰጣችሁዋለን ይለናል ይላል።
ሰርቫይቫል ኢነትረናሽናል ዳይሬክተር የሆኑት ስቲቨን ኮሪ ይህ አዲሱ መረጃ መንግስት ሊደብቀው የፈለገው ነገር እንደነበር ያሳያል። በዚያች አገር መንግስትን በሚቃወሙት ላይ ሁሉ የሚወሰደውን እርምጃ እንድናይ አደርገናል። መንግስት የዜጎችን የሰብአዊ መብቶች አያከብሩም ብለዋል።
___________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________
ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.
ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide