መጋቢት 4 ቀን 2004 ዓ/ ም
ኢሳት ዜና:-ከመምህራን የተነሳበትን ተቃውሞ ለማብረድ መንግስት በትናንትነው እለት በእያንዳንዱ ደረጃ ላይ ለሚገ መምህራን አንድ እርከን የደሞዝ ጭማሪ ማድረጉን አስታውቋል።
ጭማሪው የመንግስትን አቅም ባገናዘበ መልኩ የተፈጸመ መሆኑን መንግስት ተናግሯል። አንድ እረክን ጭማሪ ማለት 50 ብር እስከ 80 ብር የሚያካትት ነው።
መምህራን ለኢሳት እንደገለጡት ግን ጭማሪው በቀን ከ1 ብር ከ50 ሳንቲም አካባቢ ነው፤ ይህም መጠን አንድ ብርጭቆ ሻሂ እንኳን ለመጠጣት አያስችልም፣ ምክንያቱም አንድ ብርጭቆ ሻ 2 ብር ከ50 ሳንቲም ነውና ብለዋል።
በኢትዮጵያ ከሚገኙ 700 ሺ የመንግስት ተቀጣሪዎች ውስጥ 50 በመቶ አክሉ መመህራን ናቸው። የመምህራንን የደሞዝ ጭማሪ ተከትሎ የእቃዎች ዋጋም ይጨምራል ተብሎ ተስግቷል። የዚህን ዜና ሙሉ ዝርዝር በነገው ዘገባ እናቀርባለን።
በኢትዮጵያ በምግብ ፍጆታ ዕቃዎች ላይ የሚታየዉ የዋጋ ግሽበት በማደግ ላይ እንደሆነ ሮይተርስ የዜና ወኪል ገለፀ
ሮይተርስ ባገኘዉ ይፋ መረጃ መሰረት ባለፈዉ የካቲት ላይ የነበረዉ 32 በመቶ የዋጋ ግሽበት በአንድ ወር ጊዜ ዉስጥ ወደ 36.3 በመቶ ማሻቀቡን አስታዉቋል።
በጥር ወር ላይ ግምት ዉስጥ በማይገባ ደረጃ በምግብና ምግብ ነክ ባልሆኑ የፍጆታ እቃዎች ላይ ታይቶ የነበረዉ የዋጋ ግሽበት ቅናሽ በየካቲት ወር ላይ በተቃራኒዉ ከፍተኛ እድገት ማሳየቱ ተገልጿል።
ባለፈዉ 2011 አመት የካቲት ወር ላይ በምግብ ፍጆታ እቃዎች ላይ የነበረዉ የዋጋ ግሽበት ከዘንድሮዉ 2012 የካቲት ወር ጋር ሲነፃፀር 47.4 በመቶ መጨመሩንና ከምግብ ዉጭ ያሉት የፍጆታ እቃዎች ዋጋ በተመሳሳይ ወቅት በአንድ አመት ጊዜ ዉስጥ በ21.4 በመቶ ማደጉን ለማወቅ ተችሏል።
ከምግብ ፍጆታ እቃዎች ዉስጥ በእህልና ጥራጥሬ፤ በአትክልትና ፍራፍሬ እንዲሁም በቅመማ ቅመም ምርቶች ላይ ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ የተመዘገበ ሲሆን፤ በጥር ወር የነበረዉ 0.6 በመቶ የሸማች ዋጋ በአንድ ወር ጊዜ ዉስጥ በየካቲት ላይ ወደ 2 .7 በመቶ ማደጉን ሮይተርስ የዜና ወኪል ገልጿል።
ኢሳት ሰሞኑን በጤፍና በሌሎች እቃዎች ላይ የታየውን ከፍተኛ ጭማሪ መዘገቡ ይታወሳል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ለመንግስት ሰራተኞች በየወሩ 2 ኪሎ ስኳር በ30 ብር እንዲገዙ ተፈቅዶላቸዋል። በመላ አገሪቱ ከፍተኛ የስኳር እጥረት በማጋጠሙ ነዋሪዎች አንድ ኪሎ ስኳር በ30 ብር ለመግዛት እየተገደዱ ነው።
___________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________
ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.
ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide