የካቲት 28 ቀን 2004 ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-ወንጂ ስኳር በርካታ ሰራተኞችን አባረረ የህወሀት ታጋዮች ከፍተኛ የአመራር ቦታዎችን ይዘዋል
በአቶ አባይ ጸሀየ የሚመራው የስኳር ኮርፖሬሽን ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ በርካታ ሰራተኞች እየተባረሩ ነው። እስካሁን ድረስ ከ300 በላይ ሰራተኞች ያለምንም ማስጠንቀቂያና ክፍያ እንዲሰናበቱ ተደርጓል። ሰራተኞቹ በሁለት ወራት ውስጥ ቤታቸውን እንዲያስረክቡ ሲጠየቁ፣ “ልጆቻችንን የት ልንበትኗቸው ነው፣ ትምህርታቸውን እንዲያቋርጡ ለምን ታስገድዱናላችሁ የሚል ተቃውሞ አስነስተዋል። በአዲሱ ማኔጅመንት ውስጥ በሹመት የተካተቱት ነባር የህወሀት አባላት ” ሰላሳ አመት ሙሉ ቤት ያልሰራከውን አሁን ቤት ልንሰራልህ ትፈልጋለህ” የሚል መልስ በመስጠታቸው ሰራተኞቹ ቁጣቸውን ሲገልጡ እንደነበር ዘጋቢያችን አክሎ ገልጧል።
የኑሮ ውድነቱ ሰማይ በነካበት ወቅት ከስራ መባረራችን የሞት ፍርድ የተፈረደብን ያክል ተሰምቶናል በማለት አንድ ለ25 አመታት ድርጅቱን ያገለገሉ ሰው ለኢሳት ዘጋቢ ተናግረዋል።
በኢትዮጵያ ውስጥ ከፍተኛ የሆነ የስኳር እጥረት መከሰቱን መዘገባችን ይታወሳል።
___________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________
ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.
ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide