የኢትዮጵያ ሙስሊሞች መጅሊስ እኛን አይወክለንም፣ አህባሽን እና ኢህአዴግን ግን ሊወክል ይችላሉ አሉ

የካቲት 19 ቀን 2004 ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-በአወሊያ መስጊድ ከቀኑ 3፡00 እስከ 10፡00 ሰዓት ድረስ ለሰባት ሰዓታት በቆየው በዚህ የተቃውሞ ሰልፍ በመንግስትና በመጂሊስ ላይ ያነጣጠሩ ጠንካራ ተቃውሞዎች ተስተጋብተዋል።

 ይሁንና፤ በመስጊዱ ውስጥ “መጅሊስ አይወክለንም፣ ኮሚቴው የማያውቀውና ከእውቅናው ውጪ የሆነው “ኢህአዴግም አይወክለንም” የሚሉ በርካታ በኤ 4 መጠን የተባዙ ወረቀቶችለምዕመኑ መበተናቸውና  በተለያዩ ቦታዎች ተለጥፈው መታየታቸው፤በተቃውሞው ማሰማቱ ሂደት ላይ እንቅፋት ፈጥሮ ነበር።

  የተቃውሞ ወረቀቱ ከ እውቅናቸው ውጪ ድንገት ተለጥፎ በመገኘቱና በመበተኑ ግር የተሰኙት የኮሚቴ አባላት በድምጽ ማጉሊያ ለሙስሊሙ ማህበረሰብ የማሣሰቢያ  ንግግር  አድርገዋል፦ ” ኮሚቴው ያላወቃቸው ሰዎች፤ ምናልባትም የመጅሊስና የኢህአዴግ ሰዎች ሰላማዊ ትግላችንን ለመቀልበስ መወንጀያ የሚሆናቸውን ተንኮል እየሰሩብን ስለሆነ አካባቢያችሁን አጽዱ!”በማለት።

ከጁምዓ ጸሎትና ሥግደት በኋላም በኢትዮጵያ ሙስሊም ማህበረሰብና በተመረጠው ኮሚቴ አባላት መካከል   ምክክር ተደርጓል።

በዚህ ውይይት ላይ የኮሚቴው አባላት የህወሃት ኢህአዴግ ንብረት የሆነው ራዲዮ ፋና በሃቀኝነት መረጃ አደርሳለሁ ብሎ  ቃለመጠይቅ ካደረገን በኋላ ፤ሆን ብሎ  የእኛን ንግግር እየቆረጠና የመጅሊሱን ሰዎች ሰፊ ሽፋን እየሰጠ፤እንዲሁም እኛ በተናገርነው ላይ እነርሱ መልስ እንዲሰጡ እያደረገ ፕሮግራም ሳይሆን ፕሮፓጋንዳ ሰርቶብናል በማለት ክስ አሰምተዋል።

የራዲዮ ፋና አሻጥር በዚህ ብቻ አልቆመም ያሉት የሙስሊሙ ማህበረሰብ አባላት፤ ከመንግስት ጋር በመደራደር መጅሊሱ ፈርሶ ሌላ ነፃ መጅሊስ እንዲቋቋም ያደርጉ ዘንድ የተመረጡት የኮሚቴው አባላት ንግግራቸውን ሲጀምሩ ፤ ሰርጭቱ አዲስ አበባን አልፎ እንዳይደመጥ ሆን ብሎ አሻጥር መስራቱን ደርሰንበታል ብለዋል።

የመጅሊሱና የመንግሥት ተወካዮች ንግግር  የተላለፈው ግን ፤በራዲዮ ፋና አገር አቀፍ ሥርጭት እንደሆነ፤እነኚሁ የሙስሊሙ ማህበረሰብ አባላት አመልክተዋል።

የመጅሊሱና  የመንግሥት ድርጊት ሙስሊሙ ተስፋ ቆርጦ ወዳልተፈለገ ብጥብጥ እንዲያመራ ነው ያለው  የብዙሀኑ ሙስሊም አስተባባሪ ኮሚቴ፤ ” እኛ በሰጡን ቀጠሮ መሠረት እስከ የካቲት 26 ቀን 2004 ዓ.ም ድረስ ትዕግስት እናድርግና ምላሻቸውን እናድምጥ፤ ከዚያ ስለሚሆነው ሁኔታ ህዝቡ ይወስናል” ብሏል፡፡

ከአዲስ አበባ እና አካባቢዋ ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ጀምሮ የተሰባሰበው ከመቶ ሃያ ሺህ በላይ የሙስሊም ማህበረሰብ ፤ከቀኑ 10፡30 ሰዓት ላይ ቀስ እያለ ተበትኗል፡፡

3    90 በመቶ በሚሆነው የአዲስ አበባ ክፍል፤ ውሀ ተቋረጠ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ለኢሳት ዘጋቢ እንደገለጡት፤ ላለፉት ሁለት ቀናት ውሀ የሚባል ነገር ሊያገኙ አልቻሉም። በአሁኑ ጊዜ በሸራተን፣ በጥቁር አንበሳ  አካባቢ እና በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ፤ ውሀ በቦቴ እየተከፋፈለ ነው። የውሀ መቋረጡ የተፈጠረው ከለገዳዲ ወደ ጃን ሜዳ የሚሄድና ከፍተኛ ግፊት ያለው ቧንባ ላይ በተፈጠረ ችግር መሆኑን የመንግስት የመገናኛ ብዙሀን ገልጠዋል።

የአፍሪካ መዲና በሆነችው አዲስ አበባ  የውሀ ችግሩ ተባብሶ እንደቀጠለ በተደጋጋሚ መዘገባችን ይታወሳል።

___________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________

ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.

ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide