በአፋር ክልል ያለው ውጥረት እየተባባሰ ነው

(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 22/2011)በአፋር ክልል ያለው ውጥረት እየተባባሰ መምጣቱ ተገለጸ።

ፋይል

በተለይ ከውጭ እየገባ በክልሉ ላይ ጥቃት የሚያደርሰው የታጠቀ ሃይል እየተጠናከረ መምጣቱንም የአፋር የሰብአዊ መብቶች ድርጅት ሊቀመንበር አቶ ጋአስ አህመድ ለኢሳት ገልጸዋል።

እንደ እሳቸው አባባል የክልሉ መንግስትም ሆነ የፌደራል መንግስቱ በክልሉ እየደረሰ ያለውን ጉዳት ለመከላከል ምንም እየሰሩ አይደሉም ብለዋል።

በኢትዮ-ጅቡቲ መስመር የክልሉ ልዩ ሃይል ሲነሳ መከላከያ የአካባቢውን ሰላም ይጠብቃል በሚል ነበር ነገር ግን ያ ሳይሆን ቀርቷል ይላሉ።

በዚህ ሰሞን እንኳን ከጅቡቲ 12 ላንድ ክሩዘሮች ወታደር ጭነው ገብተው ከፍተኛ ጦርነት በአርብቶ አደሩ ላይ አድርገዋል።

በአካባቢውም ሰላማዊ ሰዎችን ገለው ሲሄዱ የጠየቃቸው ወይንም ሁኔታው እየከበደ መምጣቱን የሚናገር አካል አልተገኘም።

ከውጭ የሚገባው ሃይል የአፋር ህዝብን ብቻ ሳይሆንኢትዮጵያን ሊያተራምስ የሚችል ሃይል ነው ሲሉ ስጋታቸውን ይገልጻሉ አቶ ጋአስ።

ለክልሉ መንግስትም ሆነ ለፌደራል መንግስቱ ያለው ስጋት ቢነገራቸውም ርምጃ መውሰድ ግን አልቻሉም ብለዋል።