(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 25/2011)በአማራ ክልል ለተፈናቃዮች ድጋፍ የሚያሰባስበው ኮሚቴ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተሰጠውን 4.7 ሚሊዮን ብር አልቀበልም አለ።
በክልሉ ለሚገኙ ተፈናቃዮች ድጋፍ የሚያሰባስበው ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ አገኘሁ ተሻገር በሰጡት መግለጫ “ለአማራ ሕዝብ የገባው ቃል ከባንኩ የምንጠብቀው ባለመሆኑ ኮሚቴው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቃል የገባውን ገንዘብ አይቀበልም” ሲሉ ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ለሚገኙ ተፈናቃዮች 100 ሚሊዮን ብር መለገሱን አስታውቆ ነበር።
90 ሺሕ ተፈናቃዮች የሚገኙበት የአማራ ክልል ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ድጋፍ 4.7 ሚሊዮን ብር ቃል ተገብቶለታል። ባንኩ ለሶማሌ ክልል 35 ሚሊዮን ብር ፤ለኦሮሚያ ክልል 33.6 ሚሊዮን ብር ለደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክልል 18.3 ሚሊዮን ብር ሰጥቷል።
‹‹ድጋፉ የሕዝቡን ችግር ያላገናዘበ፣ በዘላቂ ለማቋቋም ለምናደርገው እንቅስቃሴ የማይመጥን ሆኖ በማግኘታችን ድጋፉን እንደማንቀበል እናሳውቃለን፡፡›› ሲሉ በአማራ ክልል የተፈናቃዮች ገቢ አሰባሳቢ ኮሚቴ ሰብሳቢ ይፋ አድርገዋል።
በክልሉ ለሚገኙ ተፈናቃዮች ድጋፍ የሚያሰባስበው ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ አገኘሁ ተሻገር በሰጡት መግለጫ “ለአማራ ሕዝብ የገባው ቃል ከባንኩ የምንጠብቀው ባለመሆኑ ኮሚቴው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቃል የገባውን ገንዘብ አይቀበልም” ሲሉ ገልጸዋል።
ይህን ድጋፍ ግን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የአማራ ተፈናቃዮች ያሉበትን አስከፊ ሁኔታ ከግምት ውስጥ ያላስገባ በመሆኑ አንቀበልም፡፡ ሕዝባዊ ወገንተኝነቱንና ካለው ካፒታል አንፃር ኃላፊነቱን ባለመወጣቱ አዝነናል›› ብለዋል አቶ አገኘሁ፡፡
የአማራ ክልል ሕዝብ ሀገሪቱ በለውጥ ንቅናቄ ውስጥ በነበረችባቸው አስቸጋሪ ወቅቶች ሳይቀር ባንኩ ላይ በአመኔታ በመቆጠብ ከፍተኛውን ሚና ሲጫወት መቆየቱን ያስታወሱት አቶ አገኘሁ ‹‹በባንኩ ላይ አደጋ እንዳይደርስ ተገቢውን ጥበቃ እያደረገ የነበረ ታማኝ ሕዝብ በመሆኑ ባንኩ ከሚያገኘው ትርፍ አንፃር ለሕዝቡ የከፋ ችግር አስፈላጊውን ድጋፍ በመስጠት ግንባር ቀደም መሆን ነበረበት›› ብለዋል፡፡
‹‹ በመሆኑም አሉ›› አቶ አገኘሁ ‹‹በመሆኑም ድጋፉ የሕዝቡን ችግር ያላገናዘበ፣ በዘላቂ ለማቋቋም ለምናደርገው እንቅስቃሴ የማይመጥን ሁኖ በማግኘታችን ድጋፉን እንደማንቀበል እናሳውቃለን›› ብለዋል፡፡
‹‹የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች በግላቸው የሚያደርጉትን ድጋፍ በአማራ ክልል ሕዝብ ሥም እናመሰግናለን›› ብለዋል፡፡
በአማራ ክልልና ከክልሉ ውጭ በተፈጠሩ ጊዜያዊ ግጭቶ ከ90 ሺህ በላይ ዜጎች ተፈናቅለው መጠለያ ውስጥ ይገኛሉ፡፡ መንግሥት እና ሕዝቡ በየወቅቱ የሚያደርጓቸው ድጋፎችም በቂ አለመሆናቸውን እና ዘላቂነት እንደሌላቸው ተፈናቃዮች እያሳሰቡ ነው፡፡ ይህን ተከትሎ ተፈናቃዮችን በዘላቂነት ለማቋቋም በሚደረገው ጥረት በአዲስ አበባ እና በአማራ ክልል እንዲሁም የአማራ ክልል ወዳጆች ድጋፍ እያደረጉ ይገኛሉ፡፡
ተፈናቃዮችን በዘላቂነት ለማቋቋም 1 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር እንደሚያስፈልግ ሲገለጽ ቆይቷል፡፡
በክልሉ የተፈናቀሉ ዜጎችን ለመርዳት በተደረገ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሀ-ግብር (ቴሌቶን) ከ700 ሚሊዮን ብር በላይ ቃል ተገብቷል፡፡ የኮሚቴው ሰብሳቢ ተፈናቃዮቹ ካሉበት ሁኔታ አንፃር በአስቸኳይ ወደ መደበኛ ሥራቸው እንዲገቡ ቃል የገቡ ድርጅቶች እና ግለሰቦች ቃል የተገባውን እንዲያሰባስቡም አቶ አገኘሁ አሳስበዋል፡፡