የስደተኞች ጉዳይ ኮሚሽን አዋጅን በመቃወም ነገ ሰልፍ ሊካሄድ ነው

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 22/2011)በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በቅርቡ የጸደቀውን የስደተኞች ጉዳይ ኮሚሽን አዋጅን በመቃወም በነገው ዕለት በሁለት ከተሞች ሰልፍ ሊካሄድ መሆኑ ተገለጸ።

ፋይል

የጋምቤላ ክልልን ነዋሪዎች ህልውና አደጋ ላይ የሚጥል ነው በሚል ተቃውሞ የሚካሄድባቸው ከተሞች አዲስ አበባና ጋምቤላ መሆናቸውን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

የተቃውሞ ሰልፉ አስተባባሪ አቶ ፔን ኡጁሉ ለኢሳት እንደገለጹት ከክልሉ ነዋሪዎች ቁጥር በላይ ለሆኑት የደቡብ ሱዳን ስደተኞች የተሰጠው መብት የኢትዮጵያውያኑን መብትና ጥቅም ከግምት ያስገባ አይደለም።

ስደተኞቹ በክልሉ የደህንነትና የጸጥታ ችግር በመፍጠር ብዙ ጉዳት ካስከተሉ ግጭቶች ጋር የሚነሱ ናቸው የሚሉት አቶ ፔን አዋጁ ይበልጥ የደህንነት ስጋት የሚፈጥር ነው ብለዋል።