(ኢሳት ዲሲ–ጥር 16/2011)የማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊካ ስፖርት ሚኒስትር የነበሩት ፓትሪክ ኤድዋርድ ናጊሶና ለዓለም አቀፉ የጦር ወንጀለኞች ፍርድ ቤት ተላልፈው ተሰጡ።
የቀድሞው የማዕከላዊ አፍሪካ ባለስልጣን እና የአፍሪካ እግር ኳስ ኮን ፌዴሪሽን አባል የነበሩትን ተጠርጣሪ ለአለም አቀፉ ፍርድ ቤት አሳልፋ የሰጠችው ፈረንሳይ መሆኗን ቢቢሲ ዘግቧል።
ግለሰቡ ባለፈው ወር ፓሪስ ላይ መያዛቸው ይታወሳል ።
ፓትሪስ ኤድዋርድ ናጊሶና የተባሉት የማዕከላዊ አፍሪካ የስፖርት ባለስልጣን ከወር በፊት ፓሪስ ላይ በቁጥጥር ስር የዋሉት በሃገሪቱ ከ4 ዓመት በፊት በተካሄደውና ሃይማኖትን መሰረት ባደረገው ጥቃት ተዋናይ ሆነው በመገኘታቸው እንደሆነም ተዘግቧል።
የማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ሃገሪቱ ነጻነቷን እንዳገኘች የሃገሪቱ ፕሬዝዳንት የነበሩት ዴቪድ ዳኮ በጃንበዲል ቦካሳ በ5 ዓመት ግዜ ውስጥ ግልበጣ ከተደረገባቸው ጊዜ ጀምሮ በየጊዜው በሚያገረሽ ቀውስ ስትናጥ ኖራለች።
በዚህች ሃገር ከ5 ዓመት በፊት የተፈጠረው ሁኔታ ለኤድዋርዶ ናጊዋና መታሰር ምክንያት ሆኗል።
እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2013 በማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ የተፈጠረውን ቀውስ ተከትሎ በዋናነት በሙስሊሞች የሚመራ ሴሌካ የተባለ የሽምቅ ቡድን የሃገሪቱን ስልጣን ያዘ።
በአብዛኛው ክርስቲያኖች በሚኖሩበት ሃገር በሙስሊሞች የሚመራ የሃይል እንቅስቃሴ ወደ ስልጣን ሲወጣ ባላካ የተባለ የክርስቲያኖች እንቅስቃሴ በተቃውሞ ተንቀሳቀሰ።
በዚህም በተከሰተው ግጭት በሺዎች የሚቆጠሩ ተገደሉ።
5 ሚሊየን ያህል ሕዝብ የማይኖርባት ሴንትራል አፍሪካ ከአንድ ሚሊየን የሚበልጥ ሕዝብ ተፈናቀለባት ሲል ቢቢሲ በዘገባው አስፍሯል።