(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 15/2011)ኢንዶኔዥያን በመታው አውሎ ንፋስ የሞቱት ሰዎች ቁጥር ወደ 300 ሲያሻቅብ የቆሰሉት ሰዎች ቁጥር ደግሞ ከ1ሺህ መብለጡ ታወቀ።
በደርዘን የሚቆጠሩ ሰዎች ደግሞ የደረሱበት አልታወቀም።
በእሳተጎመራና በመሬት መደርመስ ጭምር የተዘጋው አውሎ ነፋስ የሙዚቃ ኮንሰርት በማሳየት ላይ የነበሩ ሙዚቀኞችን ጭምር ከመድረክ ጠርጎ ሲሄድ ታይቷል፣ ህንጻዎችም ፈራርሰዋል።
265 ሚሊዮን ያህል ሕዝብ የሚኖርባትና 17ሺህ ያህል ደሴቶች የሚገኙባት ኢንዶኔዢያ በሳምንቱ መጨረሻ በገጠማት አደጋ ዋነኛው ተጠቂ ስፍራ ሳንዳስትሬት የተባለው እንደሆነም ታውቋል።
ጃሻ እና ሳማርታ በተባሉት ደሴቶች መካከል ላይ በገጠመው በመብረቅና በዝናብ የታገዘው አውሎ ነፋስ ከመነሳቱ በፊት በሬክተር ስኬል 5 ነጥብ1 የሆነ የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱንም የጀርመን ጂኦሳይንስ ማዕከል አስታውቋል።
የመሬት መንቀጥቀጥን ተከትሎ ዝናብ የቀላቀለውና በመብረቅ የታገዘው አውሎ ነፋስ በመሬት መደርመስ፣ እንዲሁም በእሳተ ጎመራ መታገዙም ታውቋል።
በሬክተር ስኬል ከ6 በላይ ይበልጣል ተብሎ በተመዘገበ ርዕደ መሬት በየአመቱ እንደምትጠቃ በባለሙያዎች የሚነገርላት ኢንዶኔዢያ እየተገባደደ ባለው የፈረንጆቹ 2018 ብቻ ዘጠኝ የታወቁ የመሬት መንቀጥቀጦችን አስተናግዳለች።
በአለም ከፍተኛውንና በሬክተር ስኬል 9.1 የተመዘገበውን ርዕደ መሬት ያስመዘገበችውም በደቡብ ኢሲያ የምትገኘው ኢንዶኔዢያ መሆኗም ታውቋል።
የዛሬ 14 ዓመት እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር ታህሳስ 26/2004 የኢንዶኔዥያዋ ሰማርታ ደሴትን የመታው የዓለማችን ከፍተኛው የመሬት መንቀጥቀጥ ከኢንዶኔዢያ አልፎ በበርካታ ሃገራት ላይ ባደረሰው ጉዳት በአጠቃላይ 230 ሺህ ያህል ሰዎች ማለቃቸውንም ይፋ የሆኑ መረጃዎች አመልክተዋል።