በቤንሻንጉል በነዋሪዎች ላይ ጥቃት እየደረሰ ነው ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–ሕዳር 7/2011)ቤንሻንጉል ክልል ካማሽ ዞን ያሶ ወረዳ በሚገኙ 9 ቀበሌዎች በሚገኙ ነዋሪዎች ላይ ከማክሰኞ ጀምሮ ጥቃት እየደረሰ መሆኑን የኢሳት ምንጮች ገለጹ።

በነዋሪዎቹ ላይ ጥቃት የደረሰው ማንነታቸውን መሰረት በማድረግ ከአካባቢው ውጡልን በሚል ነው።

ፋይል

በጥቃቱ ቁጥሩ ያልታወቀ ሰው ሲገደል በንብረት ላይም ጉዳት ደርሷል ተብሏል።

በቤንሻንጉል በተለይ በአማራና በኦሮሞ ተወላጆች ላይ ያነጣጠረ ጥቃት መካሄዱን የአካባቢው ምንጮች ለኢሳት ገልጸዋል ።

በተለይ ደግሞ በሴቶች እና አቅመ ደካሞች ላይ ጥቃቱ በርትቷል ነው የተባለው ።

የጥቃቱ አድራሾች የታጠቁ የአካባቢው ሰዎች ሲሆኑ ምክንያታቸው ደግሞ ከመሪታችን ውጡ በሚል እንደሆነ ነው የተነገረው።

ጥቃት የደረሰባቸው ሰዎች የድረሱልን ጥሪ እያቀረቡ ሲሆን የመከላከያም ሆነ የፌደራል ሃይል እንዳልደረሰላቸው ምንጮቹ ጨምረው ገልጸዋል።

በቤንሻንጉል ባላፈው ጊዜ የአካባቢው ታጣቂዎች በኦነግ ስም ከሚንቀሳቀሱ ሃይሎች ጋር በተፈጠረ ግጭት ከ70 ሺህ በላይ ሰው መፈናቀሉ ይታወሳል።

የዚሁ ጥቃት ሰበብ የሆነው ደግሞ የካማሽ ዞን 4 አመራሮች የጸጥታ ስብሰባ ላይ  ቆይተው ሲመለሱ ባልታወቁ ሰዎች በመገደላቸው እንደነበር አይዘነጋም።

አሁን ደግሞ ካማሽ ዞን ያሶ ወረዳ በሚገኙ 9 ቀበሌዎች በሚገኙ ነዋሪዎች ላይ ከማክሰኞ ጀምሮ ጥቃት እየደረሰ መሆኑን የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል።

በነዋሪዎቹ ላይ ጥቃት የደረሰው ማንነታቸውን መሰረት በማድረግ ከአካባቢው ውጡልን በሚል ነው።

በጥቃቱ ቁጥሩ ያልታወቀ ሰው ሲገደል በንብረት ላይም ጉዳት ደርሷል ተብሏል።