የመከላከያ አባላት የተቃውሞ ሰልፍ አደረጉ
( ኢሳት ዜና መስከረም 30 ቀን 2011 ዓ/ም ) የሰራዊቱ አባላት የተለያዩ የደሞዝና የመብት ጥያቄዎችን ይዘው ከጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድ ጋር መወያየታቸው ታውቋል። ወታደሮቹ እስከ እነ ትጥቃቸው ቤተመንግስት ለመግባት ጥያቄ አቅርበው የነበረ ሲሆን፣ በመንግስት በኩል ግን ወታደሮቹ ከእነ መሳሪያቸው እንዳይገቡ ተነግሮአቸዋል። እነዚህ 240 የሚሆኑ ወታደሮች፣ የቡራዩን ግጭት ለማቆጣጠር የመጡና ወደ ሃዋሳ ምድባቸው ሲመለሱ፣ እግረ መንገዳቸውን ጥያቄያቸውን ለማቅረብ መፈለጋቸውን የፖሊስ ኮሚሽነር ዘይኑ ጀማል ለአሜሪካ ድምጽ ተናግረዋል።
ወታደሮቹ ከውይይት በኋላ ከጠቅላይ ሚንስትሩ ጋር ፎቶ ተነስተዋል፡፡