የኢትዮጵያ እና የኤርትራ የሰላም ስምምነት የስደተኞችን ወደ አገራቸው ለመመለስ ያፋጥነዋል ተባለ።
( ኢሳት ዜና መስከረም 30 ቀን 2011 ዓ/ም ) ድንበር አቆራርጠው ወደ እስራኤል የሚገቡ ሕገወጥ ስደተኞችን ፍልሰት ለማስቆም የድንበር አጥር ከለላን ጨምሮ ስደተኞችን ወደ ትውልድ አገራቸው ለመላክ የኢትዮጵያ እናየኤርትራ የሰላም ስምምነት ማድረጋቸው ሁኔታዎችን ያፋጥነዋል ሲሉ የእስራኤል ጠቅላይ ሚንስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ አስታወቁ ። የግራክንፍ ፖለቲከኞች ተቋርጦ የነበረውን ስደተኞችን ወደ አገራቸው የመመለስ ስራን ዳግም እንዲቀጥል ይፈልጋሉ ሲል ሃሬትዝ ዘግቧል።