(ኢሳት ዲሲ–መስከረም 25/2011) በፊልምና ቴአትር ላይ ይደረግ የነበረው ቅድመ ገምገማ ተነሳ ።
የአዲስ አበባ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ዛሬ በደብዳቤ እንዳሳወቀው ቅድመ ግምገማውን ይደግፉ የነበሩ አሰራሮችና መመሪያዎች ከህገመንግስቱ በታች ስለሆኑ ከመከረም 26 ጀምሮ አሰራሩ መነሳቱን አሳውቋል።
በአዲስ አባባ በህልና ቱሪዝም ቢሮ ሃላፊ በረዳት ፕሮፌሰር ነብዩ ባዮ ፊርማ የወጣው ደበዳቤ እንደሚናገረው የፊርማና የግል የቴአትር ስራዎች ከመታየታቸው በፊት ተገምግመው ማሳያና ማሰራጫ ፈቃድ ያላገኙ ፊልምና ቴአትሮች አይቀርቡም ነበር ።
ይህ አሰራር የህገመንግስቱን አንቀጽ 29 ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብትን የሚጻረር መሆኑን በመጥቀስ ፣ በሌላ በኩልም ግምገማው ወጥነት የሌለውና በፊልምና ቴአትር ስራዎች ላይ ብቻ ያተኮረ በመሆኑ ግምገማው መነሳቱን ገልጿል።
ቢሮው ግምገማው በምን ላይ ያተኩር እንደነበር የገለጸው ነገር የለም።
ቅድመ ግምገማውን ተከትሎ የዘርፉ ባለሙያዎች አስተያየት የሰጡ ሲሆን የዘርፉ ሙያተኞች እንደጋዜጠኛ የመታሰር፣ የመሰደድ የገንዘብ ቅጣት ባይደርስባቸውም የነበረባቸውም ጫና ከሌሎች የኪነጥባበ ሙያዎች አንጻር ከባድ እንደነበር አንስተዋል።