(ኢሳት ዲሲ–መስከረም 24/2011) የሲዳማ አርነት ንቅናቄ/ሲአን/ አመራሮች በመንግስት የተደረገውን ጥሪ ተቀብለው ዛሬ ኢትዮጵያ መግባታቸው ታወቀ።
በሲአን የውጭ ግንኑነት ሃላፊ በአቶ ደምቦባ ኪያናቴ የተመራው የልኡካን ቡድን ዛሬ አዲስ አበባ ሲገባ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ፕሮፌሰር አፈወርቅ ካሱ ተቀብለዋቸዋል።
የሲዳማ አርነት ንቅናቄ ከዛሬ 40 አመት በፊት የመብት ጥያቄ አንስተው በትጥቅ ትግል ከሚንቀሳቀሱ ሃይሎች አንዱ እንደነበር ይታወቃል።
ሴአን የሽግግር መንግስቱ አባልና በኋላም እንደ ኦነግ ሁሉ ተገፍቶ ከሽግግር መንግስቱ ተገፍቶ መውጣቱ ይታወቃል።
የድርጅቱ ሊቀመንበር የነበሩትም አቶ ወልደአማኑኤል ዱባለ በስደት ለንደን ውስጥ ቆይተዋል።
በ1997 ከመንግስት ጋር ተደራድረው ወደ ሃገር ሲመለሱ ሌሎቹ አመራሮች አይወክሉንም በማለት ትግላቸውን ቀጥረዋል።
የሲአን መስራችና መሪ የነበሩት አቶ ወልደአማኑኤል ዱበላም ኢትዮጵያ በተመለሱ በጥቂት አመታት ሕይወታቸው ማለፉ ይታወሳል።