በቦረና አካባቢ ኦነግ ህዝቡን የጦር መሳሪያ እያስታጠቀ አለመረጋጋት እየፈጠረ ነው
( ኢሳት ዜና መስከረም 23 ቀን 2011 ዓ/ም ) የአካባቢው ነዋሪዎች ለኢሳት እንደገለጹት በቡሌ ሆራና በአካባቢው የሚንቀሳቀሱ የኦነግ ታጣቂዎች፣ “ የቀድሞ ስርዓት ናፋቂዎች ተመልሰው ስልጣን የሚይዙ በመሆናቸው ትጥቃችን አንፈታም” በማለት ህዝቡን ሰብስበው በማናገርና ወጣቶችን እየመለመሉ በማስታጠቅላይ ናቸው። ለደህንነታቸው በመስጋት ስማቸው እንዳይገለጽ የጠየቁ ሰዎች እንደተናገሩት፣ የታጣቂዎች ቁጥር በየጊዜው እየጨመረ በመምጣቱ ህዝቡ ስጋት ላይ ወድቋል።
መንግስት እስካሁን እርምጃ ለምን እንዳልወሰደ ጥያቄ የሚያቀርቡት ነዋሪዎች፣ እነሱን የማይቀበሉትን ሁሉ ወደ ጫካ በመውሰድ እያሰሩ ናቸው። የኦህዴድ ከፍተኛ ባለስልጣን የሆኑት አቶ አዲሱ አረጋ ሰሞኑን በኦነግስም የሚንቀሳቀሱ ሃይሎች ትጥቅእንዲፈቱ ካልፈቱግን መንግስት በሃይል እንደሚያስፈታቸው መናገራቸው ይታወቃል።
የኦነግ ታጣቂዎች ብዙዎቹ በኬንያና ኢትዮጵያ ድንበር አካባቢ የሚንቀሳቀሱ ናቸው።