ከቡራዩ ለተፈናቀሉ ወገኖቻቸው ድጋፍ ለማግኘት የተንቀሳቀሱ 35 ወጣቶች ታሰሩ
( ኢሳት ዜና መስከረም 11 ቀን 2011 ዓ/ም ) 35 የጨርቆስና እና አካባቢው ወጣቶች ከቡራዩ ለተፈናቀሉ ሰዎች ድጋፍ ለማድረግ ሲንቀሳቀሱ በፖሊስ ቁጥጥር ስር መሆናቸውንና ይህ ዘገባ እስከተጠናከረበት ጊዜ ድረስ በሰንዳፋ እንደሚገኙ ቤተሰቦቻቸው ለኢሳት ተናግራል።
ወጣቶቹ ከአካባቢያቸው በሰበሰቡት ገንዘብ የገዟቸውን ምግብ እና ቁሳቁሶች አስረክበው ሲመለሱ ፣ የኮልፌ ቀራንዮ ፖሊስ ምግብ እና ቁሳቁስ ጭነውበት ከነበሩት 3 መኪኖች ጋር በቁጥጥር ስር አውለዋቸዋል።
በጉዳዩ ዙሪያ የአዲስ አበባ ፖሊስን አስተያየት ለማግኘት ተደጋጋሚ የስልክ ሙከራ ቢደረግም አልተሳካም።