የቀድሞውን የድህንነት አዛዥ ለመያዝ ክትትል እየተደረገ ነው
( ኢሳት ዜና ነሐሴ 18 ቀን 2010 ዓ/ም ) ከሰኔ 16 ቀን 2010 ዓም የመስቀል አደባባይ ፍንዳታ ጋር በተያያዘ የቀድሞው የደህንነት ሚኒስትር የነበሩት አቶ ጌታቸው አሰፋን ለመያዝ ክትትል እየተደረገ መሆኑን ምንጮች ገልጸዋል። የእስር ማዘዣ መውጣቱን ተከትሎ፣ የህወሃት ባለስልጣናት ግለሰቡን በሱዳን በኩል ከአገር እንዲወጡ አድርገዋቸዋል የሚል እምነት በመንግስት ባለስልጣናት ዘንድ ያለ ሲሆን፣ ያሉበትን ቦታ ግን እስካሁን በትክክል ለማወቅ አልተቻለም። የኢትዮጵያ የጸጥታ ሃይሎች ግለሰቡን ለመያዝ ክትትላቸውን መቀጠላቸውንም ምንጮች ገልጸዋል።
አቶ ጌታቸው አሰፋ ከፍንዳታው ጋር በተያያዘ እጃቸው እንዳለበት የሚያሳዩ መረጃዎች የተገኙባቸው ሲሆን፣ በእርሳቸው ትዕዛዝ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የጦር መሳሪያዎች ከቦታ ቦታ ሲዘዋወሩ መያዛቸውንም ምንጮች ተናግረዋል።
አቶ ጌታቸው አሰፋ በኢህአዴግ የስራ አስፈጻሚ ስብሰባ ላይ አልተገኙም።