አርበኞች ግንቦት ሰባት ወደ ሀገር ቤት ሊገባ ነው

(ኢሳት ዲሲ–ሀምሌ 24/2010) አርበኞች ግንቦት ሰባት ንቅናቄ አመራሩ ሙሉ በሙሉ ወደ ሀገር ቤት እንደሚገባ አስታወቀ።

በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ የንቅናቄው አመራሮች ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ ዛሬ በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ተገልጿል።

ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ጋር በዋሽንግተን ዲሲ ውይይት መደረጉን የጠቀሰው ንቅናቄው የተጀመረውን ለውጥ ወደ ግቡ እንዲደርስ ለማድረግ ወደ ሀገር ቤት መግባቱ አማራጭ የሌለው እንደሆነ በማመን ውሳኔ ላይ መድረሱን አስታውቋል።