በአዊ ዞን የተፈጸመውን ግድያ የክልሉ መስተዳድር አወገዘ
( ኢሳት ዜና ሃምሌ 24 ቀን 2010 ዓ/ም ) በአዊ ብሄረሰብ ጃዊ ወረዳ ፈንድቃ ከተማ ላይ በዜጎች ላይ የተፈጸመውን ግድያ ያወገዘው የአማራ ክልል አስተዳደር፣ ምርመራ በማድረግ አጥፊዎችን ለህግ እንደሚያቀርብ አስታውቋል።
የክልሉ ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ዋና ዳይሬክተር አቶ ንጉሱ ጥላሁን ለአማራ ቲሌቪዥን ጣቢያ እንደተናገሩት፣ ክልሉ ብሄርን መሰረት አደርጎ የሚካሄድን ጥቃት አይታገስም።
የትግራይ ክልልም እንዲሁ ድርጊቱን አውግዞ በአጥፊዎች ላይ እርምጃ እንዲወሰድ ጠይቋል።
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የሚታዩ ግጭቶች የተጀመረውን የለውጥ እንቅስቃሴ እንዳያደናቅፉ፣ ህብረተሰቡ በተለይም ወጣቶች ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለባቸው የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጥሪ ሲያደርጉ ሰንብተዋል።