ላለፉት 12 አመታት በህወሀት ኢህአዴግ አገዛዝ በኃይል ተዘግተው ከነበሩት የነፃው ፕሬስ ቢሮዎች መካከል አንዱ የነበረው የእነ እስክንድር ቢሮ ዳግም ተከፈተ።
( ኢሳት ዜና ሃምሌ 23 ቀን 2010 ዓ/ም ) ካለፉት ስድስት ዓመታት እስር በኋላ በቅርቡ ከእስር የተፈታው ጋዜጠኛ እስክንድር በአጭር ጊዜ ውስጥ በተለያዩ የሚዲያ ውጤቶች ከህዝቡ ጋር ለመገናኘት ተግባራዊ እንቅስቃሴ ላይ ይገኛል.።
የእስክንድ ቢሮ ከ12 ዓመታት በኋላ ሲከፈት ጋዜጠኞች እና የዞን ዘጠን ጦማርያን ተሰባስበውም ኬክ በመቁረስ መልካም የስራ ዘመን ተመኝተዋል.።
በስደት አሜሪካ የምትገኘው የሰርካለም አሳታሚ ድርጅት ሥራ አስኪያጅ ባለቤቱ ሠርካለም ፋሲል ጉዳዩን አስመልክታ በሰጠችው አስተያዬት፦“.ነፃው ፕሬስ ታፍኖ አይቀርም….የህዝብ አደራ አለብን!”ብላለች።
ትናንት በሆላንድ -ደንሀግ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝን ለመቀበል በተሰናዳው ዝግጅት ላይ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ባደረገው ንግግር ከእስክንድር ነጋና ከሌሎች ጋዜጠኞች ጋር አንድ ላይ በመሆን በቴሌቬዥንና በጋዜጣ ወደ ጋዜጠኝነት ሥራው ለመቀላቀል ዝግጅት እያደረጉ መሆኑን አስታውቆ ነበር።