(ኢሳት ዲሲ–ሐምሌ 19/2010) ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ዛሬ ዋሽንግተን ዲሲ ገቡ።
ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ጋር የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ለማ መገርሳና ሌሎች ከፍተኛ ባለስልጣናትም አብረው መግባታቸው ተመልክቷል።
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ቀትር ላይ የኢንጅነር ስመኘውን አሟሟት በተመለከተ መግለጫ ይሰጣሉ ተብሎ መርሃ ግብር ተይዟል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ መግለጫውን ከሚሰጡበት ዋሽንግተን ዋተር ጌት ሆቴል የተገኘው ምናላቸው ስማቸው ከስፍራው የሚከተለውን አድርሶናል።