በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የተፈጠረው ልዩነት መቋጨቱ ተገለጸ

(ኢሳት ዲሲ–ሐምሌ 19/2010) ከሩብ ክፍለ ዘመን በላይ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተከርስቲያን አባቶች መካከል የተፈጠረው ልዩነት መቋጫ ማግኘቱ ዛሬ በይፋ ተገለጸ።

በሽምግልና ጥረቱ የተገኙት አባቶች ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ በተገኙበት ዛሬ በሰጡት መግለጫ ለሁለት የተከፈለው ሲኖዶስ ወደ አንድ እንዲመጣ ስምምነት ላይ ተደርሷል።

ከ25 አመታት በኋላ የተሰደዱት ፓትሪያርክ አቡነ መርቆሪዎስ ወደ መንበራቸው እንዲመለሱ ስምምነት ላይ ተደርሷል።

ከእንግዲህ ሁለት ሲኖዶስ እንደማይኖርና ቤተክርስቲያኒቱ በአንድ ሲኖዶስ እንደምታመራም ይፋ ተደርጓል።