በተለያዩ አካባቢዎች በሚገኙ እስር ቤቶች የእሳት ቃጠሎ ደረሰ

በተለያዩ አካባቢዎች በሚገኙ እስር ቤቶች የእሳት ቃጠሎ ደረሰ
( ኢሳት ዜና ሃምሌ 18 ቀን 2010 ዓ/ም ) ትናንት በደብረማርቆስና አርባ ምንጭ እስር ቤት ቃጠሎ ተነስቶ በንብረት ላይ ጉዳት ከደረሰ በሁዋላ፣ ዛሬ ደግሞ በወልድያ፣ ፍኖተሰላም፣ ሸዋ ሮቢትና መቀሌ እስር ቤቶች የእሳት ቃጠሎ ደርሷል። በወልድያ እስር ቤት በተከሰተው የእሳት ቃጠሎ 2 ሰዎች ሲሞቱ 3 ሰዎድ ደግሞ ቆስለዋል። በመቀሌ እስር ቤት በተነሳው ቃጠሎም እንዲሁ እስካሁን የሁለት እስረኞች ህይወት አልፏል። በሸዋ ሮቢትም ተመሳሳይ ተቃውሞ የተነሳ ሲሆን፣ ፖሊሶች በርካታ ጥይቶችን ይተኩሱ እንደነበር የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል።በቃሊቲና ቂሊንጦም ተመሳሳይ ተቃውሞ ተነስቷል።
እስረኞቹ በቅርቡ የወጣውን የምህረት አዋጅ በመቃወም ተቃውሞ መጀመራቸውን የመንግስት ባለስልጣናት ገልጸዋል።