(ኢሳት ዲሲ–ሐምሌ 17/2010) በምዕራብ ጎጃም ፍኖተሰላም በተካሄደ ስብሰባ ህዝቡ በህወሀት ላይ ከፍተኛ ቁጣ ማሰማቱ ተገለጸ።
ላለፉት 27 ዓመታት በአማራው ህዝብ ላይ የተፈጸምው ግፍና መከራ በህዝቡ በዝርዝር ተነስቶ የህወሀት አገዛዝ ላይ ውግዘት መቅረቡን ያገኘነው መረጃ ያምለክታል።
በህዝብ ላይ ይሄ ሁሉ መከራ ሲደርስ ብአዴን የት ነበረ በሚል በአመራሮቹ ላይ ተቃውሞ መሰማቱን ለማወቅ ተችሏል።
ለጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ አስተዳደር ድጋፍ ለማሳየትና ከለውጡ ለመጓዝ አስተዋጾአችን ምን መሆን አለበት በሚል ለመምከር የተጠራው ስብሰባ አጀንዳው ተቀይሮ የዓመታት ብሶት የተገለጸበት መድረክ ሊሆን መቻሉን የደረሰን መረጃ አመልክቷል።