(ኢሳት ዲሲ–ሐምሌ 2/2010) የትግራይ ክልል ምክር ቤት ሕገ መንግስቱ እየተጣሰ ነው በሚል መግለጫ አወጣ።
የክልሉ ምክር ቤት ሰሞኑን መቀሌ ያካሄደውን ስብሰባ ተከትሎ ባወጣው መግለጫ የፌደራሉ መንግስት ባንዲራ እየተቀደደና እየተቃጠለ ነው በማለት አውግዟል።
ከወሰን ጥያቄ ጋር በተያያዘ ሁከትና ብጥብጥ ለመፍጠር እንቅስቃሴ እየተደረገ ነው ያለው የትግራይ ክልላዊ መንግስት ከኤርትራ ጋር የተጀመረው ንግግር ህዝብን በሚያሳትፍ መንገድ እንዲቋጭም ጥሪ አቅርቧል።
በየክልሉ በሚካሄዱ ትዕይንተ ሕዝቦች ከኮብ የሌለበት ባንዲራ በስፋት መውለብለቡ በሕወሃት ደጋፊ አክቲቪስቶች ዘንድ ተቃውሞ ሲቀርብበት ቆይቷል።
የትግራይ ክልላዊ መንግስት ቴሌቪዥን ጣቢያም ይህንኑ ድርጊት ሲያወግዝ ቆይቷል።
ኮከብ የሌለበት ባንዲራ ተውለበለበ በሚል ቅሬታ ያቀረበ ሌላ ክልላዊ መንግስት ግን እስካሁን አልታየም።