የደቡብ ብሄሮች ብሄረሰቦች እና ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት ሰሞኑን በአካባቢው በተፈጠረው ግጭት ለጠፋው የሰው ህይወትና ለወደመው ንብረት ይቅርታ ቢጠይቅም፣ አሁንም የለውጥ እንቅፋት የሆኑ የክልሉ መስተዳድር አካላት ሕዝቡን እያማረሩ መሆናችው ተገለጸ።

የደቡብ ብሄሮች ብሄረሰቦች እና ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት ሰሞኑን በአካባቢው በተፈጠረው ግጭት ለጠፋው የሰው ህይወትና ለወደመው ንብረት ይቅርታ ቢጠይቅም፣ አሁንም የለውጥ እንቅፋት የሆኑ የክልሉ መስተዳድር አካላት ሕዝቡን እያማረሩ መሆናችው ተገለጸ።
(ኢሳት ዜና ሰኔ 22 ቀን 2010 ዓ/ም) ርዕሰ መስተዳደሩ አቶ ደሴ ዳልኬ ባለፉት ሁለት ሳምንታት በሀዋሳ ከተማና አከባቢዋ፣ እንዲሁም በለኩ፣ በይርጋለም ፣ በወንዶ ገነት ፣ በሻመና፣ በወልቂጤ፣በአማን፣ በአማሮ፣በቡረጅ እና በጉጅ ዞን አዋሳኝ፡ቦታዎች በተቀሰቀሱ ግጭቶች በሰውና በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱንና በርካቶች መፈናቀላቸውን ትናንት በሰጡት መግለጫ አውስተዋል።
ለተፈጸመው ግጭትና ለደረሰው ጥፋት የክልሉ አስተዳደር ሕዝቡን ይቅርታ መጠየቁንም ር ዕሰ መስተዳድሩ ተናግረዋል።
የማህበራዊ ትስስር ድረ-ገፅን በመጠቀም የበለጠ ግጭቱ እንዲባባስ የሚያደርጉ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ያሳሰቡት አቶእ ደሴ ፥ ህብረተሰቡ እነዚህ ወገኖች ሊታገላቸው እንደሚገባም አስታውቀዋል።
በአሁኑ ወቅት በሀገሪቱ እየመጣ ያለውን ፈጣን ለውጥ ለማደናቀፍ የተሰማሩ ወንጀለኞች ለህግ አሳልፎ የመስጠት ስራ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ሲሉም አቶ ደሴ ሕዝቡን አሳስበዋል።
ርዕሰ መስተዳድሩ ይህን ቢሉም በክልሉ መስተዳድር የተሰገሰጉ ጸረ ለውጥ ኃይሎች አሁንም ለውጡን የሚያደናቅፍ ተግባር እየሰሩ እንደሚገኙ መረጃዎች ያመለክታሉ።
በዛሬው ዕለት የዶክተር አብይን አስተዳደር የለውጥ ጅምር ለማበረታታት የድጋፍ ሰልፍ ለማድረግ የጠየቁ ወጣቶች በፖሊሶች ተደብድበው እንዲመለሱ የተደረጉ ሲሆን፣ ከፍተኛ ድብደባ የደረሰበት የአስራ ሦስት ዓመት ታዳጊ ወጣል ሆስፒታል መወሰዱ ታውቋል።
የፖሊሶቹ ድብደባ የዶክተር አብይ ምስል ያለበትን ካናቴራ በለበሱ ወጣቶች ላይ የከፋ እንደነበር የዓይን እማኞች ገልጸዋል።
ህወኃት ጠቅላይ ሚኒስትር እንዲሆኑ ድጋፍ ቢያደርግላቸውም በዶክተር አብይ የተሸነፉት ሽፈራው ሽጉጤ ከቀናት በፊት እና ወዳጃቸው አቶ ሲራጅ ፈጌሳ በአካባቢው የተከሰተውን ግጭት ተከትሎ በቅርቡ ከድርጅት ሥልጣናቸው መነሳታቸው ይታወቃል።
ከሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር ጋር በመሆን የአማራ ተወላጆችን ከጉራፈርዳ በማፈናቀል የሚከሰሱትና በከፍተኛ ሙስና መዘፈቃቸው የሚነገርላቸው ሽፈራው ሽጉጤ ለውጡ እውን ከሆነ ቢያንስ በሙስና እንደሚጠየቁ ከሚሰጉት ባለሥልጣናት መካከል አንዱ መሆናቸው ይታመናል።
በመሆኑም ባለፉት ዓመታት የዘረጓቸውን የጥቅም ሰንሰለቶች በመጠቀም በየቦታው ግጭቶች እንዲቀሰቀሱ እያደረጉ ነው በማለት ውስጥ አዋቂዎች ይከሳሉ።