ህወሃት በአዲስ አበባ የተቃውሞ ሰልፍ መጥራቱ ታወቀ

ህወሃት በአዲስ አበባ የተቃውሞ ሰልፍ መጥራቱ ታወቀ
(ኢሳት ዜና ሰኔ 8 ቀን 2010 ዓ/ም) የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት ህወሃት የኢትዮ-ኤርትራ የድንበር ስምምነትን በተመለከተ ኢህአዴግ በቅርቡ የወሰነውን ውሳኔ ለመቃወም እንዲሁን በአዲሱ ጠ/ሚኒስትር የተወሰዱ ምደባዎችን ለመቃወም የፊታችን እሁድ በአዲስ አበባ የተቃውሞ ሰልፍ ያደርጋል። ለሰለፉ ማካሄጃ ከፍተኛ ገንዘብ የተመደበ ሲሆን፣ በርካታ ሰዎች ከትግራይ ክልል በህወሃት ወጪ ወደ አዲስ አበባ መጥተው በሰልፉ ላይ እንደሚሳተፉ ምንጮች ገልጸዋል።
ዜናውን እስካጠናከርንበት ሰዓት ድረስ የሰላማዊ ሰልፍ ፈቃድ አልተሰጠም፣ ይሁን እንጅ ህወሃት ሰልፉን በጉልበት እንደሚያካሂድ ሲዝት መዋሉት የመስተዳድሩ ምንጮች ገልጸዋል።
ህወሃት በአደባባይ በባድመ ዙሪያ የተላለፈውን ውሳኔ እንደደገፈው ቢገልጽም፣ አጋጣሚውን የትግራይን ህዝብ ከጎኑ በማሰለፍ በአብይ አስተዳደር ላይ ጫና ለመፍጠር ማሳቡ ተነግሯል።