300 የሚደርሱ የፖለቲካ እስረኞች እና በሌሎች ወንጀሎች ተፈርዶባቸው የነበሩ ከእስር ተፈቱ

300 የሚደርሱ የፖለቲካ እስረኞች እና በሌሎች ወንጀሎች ተፈርዶባቸው የነበሩ ከእስር ተፈቱ
(ኢሳት ዜና ሰኔ 8 ቀን 2010 ዓ/ም) በሽብር ወንጀል ተከሰው ሞት እና የእድሜ ልክ እስራት የተፈረደባቸው 289 እስረኞች ዛሬ ከእስር ተፈተዋል። ከተፈቱት መካከል በእስር ቤት ውስጥ ጥፍሮቹ ተነቅለውና የተለያዩ የጭካኔ እርምጃዎች የተፈጸሙበት አበበ ካሴና ሌሎችም በአርበኞች ግንቦት7 ስም ታስረው የነበሩት ተለቀዋል። አበበ ካሴ በኢትዮጵያ ህዝብ ጸሎትና ትግል መፈታቱን ገልጾ ለህዝቡ ምስጋና አቅርቧል።