ከኦሮምያ ክልል የተፈናቀሉ የአማራ ተወላጆችን ወደ ቦታቸው እንደሚመልሱ አቶ ለማ መገርሳ ተናገሩ
(ኢሳት ዜና ሰኔ 8 ቀን 2010 ዓ/ም) የአማራ ክልል መገናኛ ብዙሃን እንደዘገበው የለማ አስተዳደር የተፈናቀሉትን ዜጎች ወደ ነበሩበት ቀዬ ለመመለስ ስራዎችን እየሰራ ነው።
አቶ ለማ ዜጎች እንዲፈናቀሉ ባደረጉ ባለስልጣናት ላይ እርምጃ መወሰዱንም ተናግረዋል።
የኦሮምያ ክልል የኮሚኒኬሽን ሃላፊ ዶ/ር ነገሪ ሌንጮ በባህርዳር ተገኝተው ከተፈናቀሉት ዜጎች ጋር ውይይት ማድረጋቸውን የክልሉ ሚዲያ ዘግቧል።