በጌዲዮና ጉጂ ብሄረሰቦች መካከል ያለው ግጭት ዳግም አገረሸ
(ኢሳት ዜና ግንቦት 27 ቀን 2010 ዓ/ም) ትናንት በተመጀረው ግጭት በርካታ ዜጎች ቀያቸውን እየተዉ ለመሰደድ የተገደዱ ሲሆን፣ በቆጨሬ ወረዳ ጀልዶ ቀበሌ አነድ የጌዲዮ ተወላጅ ሲሞት 1 ፖሊስ መቁሰሉ ታውቋል። 2 ትምህርት ቤቶችም በቃጠሎ ወድመዋል። ባንኮ ጎጢት፣ ባንኮ ጨልጨሌ፣ ባንኮ፣ ታታቱ እና ሌሎችም አካባቢዎች ከፍተኛ የተኩስ ለውውጥ ሲሰማ እንደነበር የሚገልጹት የአካባቢው ነዋሪዎች፣ ውጥረቱ ዛረም ድረስ የቀጠለ በመሆኑ መንግስት ጣልቃ ገብቶ ጥቃቱን እንዲያስቆም ጠይቀዋል።
በሚያዚያ ወር ተቀስቅሶ በነበረው ግጭት በርካታ ዜጎች ካለቁና ከፍተኛ ንብረት ከወደመ በሁዋላ የሁለቱ ወገኖች የአገር ሽማግሌዎች እርቅ አድርገው አንጻራዊ ሰላም ሰፍኖ ቆይቷል።