የጋምቤላ ክልል ፕሬዚዳንት ዶ/ር ጋትሎክ ቱት ውጭ አገር ሄደው እንዲታከሙ የክልሉ ካቢኔ ከክልሉ መጠባበቂያ በጀት 1 ሚሊዮን ብር ወጪ እንዲሆን ወሰነ።

የጋምቤላ ክልል ፕሬዚዳንት ዶ/ር ጋትሎክ ቱት ውጭ አገር ሄደው እንዲታከሙ የክልሉ ካቢኔ ከክልሉ መጠባበቂያ በጀት 1 ሚሊዮን ብር ወጪ እንዲሆን ወሰነ።
(ኢሳት ዜና ግንቦት 23 ቀን 2010 ዓ/ም) የክልሉ ምክር ቤት ለክልሉ ፋይናንስ ክፍል በላከው ደብዳቤ ላይ ርዕሰ መስተዳድሩ ዶ/ር ጋትሎክ ቱት ህክምናቸውን በጦር ሃይሎች ሆስፒታል ሲከታተሉ ቢቆዩም፣ ለውጥ ሊታይ ስላልቻለ ወደ ውጭ አገር ሄደው የተሻለ ህክምና እንዲያገኙ 1 ሚሊዮን ብር እንዲሰጣቸው የክልሉ መንግስት ካቢኔ በሙሉ ድምጽ መደገፉን ገልጿል።
ገንዘቡ ከመጠባበቂያ በጀት በክልሉ የግዢ የስራ ሂደት አስተባባሪ በሆኑት አቶ ማቲዎስ ገለታ ስም ወጮ ተደርጎ ለርዕሰ መስተዳደሩ እንዲከፈልም ደብዳቤው ያዛል።