በዚምባቡዌ በመጪው ሃምሌ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ሊካሄድ ነው

(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 22/2010) ዚምባቡዌ በመጪው ሃምሌ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ እንደምታካሂድ አስታወቀች።

የሃገሪቱ ፕሬዝዳንት ኤመርሰን ምናንጋግዋ እንዳሉት በሃገሪቱ የሚካሄደው ፕሬዝዳንታዊና የፓርላማ ምርጫ ግልጽ በሆነ መንገድ እንዲካሄድ አለም አቀ ታዛቢ ቡድኖችምእንዲገኙ ይደረጋል ብለዋል።

እንደ አውሮፓውያኑ ከ2002 በኋላም ለመጀመሪያ ጊዜ በጋራ የበለጸጉ ሃገራት ታዛቢ ቡድን እንዲገኝ ግብዣ እንደሚያደርጉም ምናንጋግዋ አስታውቀዋል።

በመጪው ሃምሌ ይካሄዳል የተባለው ይህ ምርጫ በሃገሪቱ የፖለቲካ ታሪክ ውስጥ ተጽእኖ ፈጣሪ የሚባሉት ሙጋቤና ሻንጋራይ ሳይገኙ የሚካሄድ የመጀመሪያ ምርጫ ይሆናል ተብሏል።

ማናንጋግዋ ወደ ስልጣን የመጡት ባለፈው ህዳር የ94 አመቱ ሮበርት ሙጋቤ በወታደራዊ ሃይሉ ከስልጣን መነሳታቸውን ተከትሎ መሆኑን ሮይተርስ በዘገባው አስታውሷል።