ዶክተር ፍቅሩ ማሩን ጨምሮ የ62 ተካሳሾች ክስ ተነሳ ክሳቸው ከተነሳላቸው መካከል 16 ተከሳሾች ወደ ዝዋይ ተወሰዱ::

ዶክተር ፍቅሩ ማሩን ጨምሮ የ62 ተካሳሾች ክስ ተነሳ
ክሳቸው ከተነሳላቸው መካከል 16 ተከሳሾች ወደ ዝዋይ ተወሰዱ::
(ኢሳት ዜና ግንቦት 03 ቀን 2010 ዓ/ም) ባለፈው ሳምንት እንዲከላከሉ የተወሰነባቸው እነ ዶክተር ፍቅሩ ፣ ፍቅረማርያም አስማማው፣ማስረሻ ሰጠኝና ሌሎችም እስረኞች ክሳቸው ተቋርጦ ከእስር ይፈታሉ::
ይሁን እንጅ ዛሬ 16 እስረኞች በከባድ ጥበቃ ውስጥ ሆነው ወደ ዝዋይ ተወስደዋል፣ከተወሰዱት መካከል አግባውሰጠኝ ፣ፍቅረማርያምና ማስረሻ በካቴና መታሰራቸውታውቋል::
እስረኞቹ ሰሞኑን ፍርድ ቤት ውስጥ ተቃውሞ በማሰማታቸው ድብደባ ተፈጽሞባቸው ነበር:: ወደ ዝዋይ የተወሰዱትም ለማሰቃየት መሆኑን የእስረኛ ቤተሰቦች ገልጸዋል ::