የአምቦ ተማሪዎች ባነሱት ተቃውሞ ተማሪዎች ወደ ሆስፒታል ተወሰዱ

የአምቦ ተማሪዎች ባነሱት ተቃውሞ ተማሪዎች ወደ ሆስፒታል ተወሰዱ
(ኢሳት ዜና ሚያዝያ 18 ቀን 2010 ዓ/ም)ተማሪዎቹ በእስር ላይ የሚገኙ ጓደኞቻቸው እንዲፈቱ ጥያቄ ያቀረቡ ሲሆን፣ ወታደሮች አስለቃሽ ጥይት በመተኮስ በትነዋቸዋል። በተኩሱ አንድ የጎንደር እና ሁለት የአምቦ ተወላጆች ተጎድተዋል። አንደኛው ተማሪ ከሆስፒታል የወጣ ሲሆን፣ ሁለቱ ግን አሁንም በህክምና ላይ ናቸው።
ተማሪዎች ጥያቄያቸው ካልተመሰለ በስተቀር ተቃውሞአቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል።
አምቦ በኢትዮጵያ ለሚካሄደው የለውጥ እንቅስቃሴ ዋነኛዋ ማእከል ናት። በቅርቡ አዲሱ ጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድ በአምቦ ተገኝተው ህዝቡ ላደረገው ትግል ምስጋና አቅርበው ነበር። ይሁን እንጅ የከተማው ህዝብ አሁንም መሰረታዊ ለውጥ እንዳልመጣ ይገልጻል። በተለይ ለብዙ ህዝብ ህይወት ህልፈት ምክንያት የሆነው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ አለመነሳቱ የከተማዋን ነዋሪዎች ያሳሰበ ጉዳይ ነው።