በጅግጅጋ ባለፈው ቅዳሜ በደረሰው የጎርፍ አደጋ እስካሁን ከ7 ያላነሰ አስከሬን መገኘቱ ታወቀ

በጅግጅጋ ባለፈው ቅዳሜ በደረሰው የጎርፍ አደጋ እስካሁን ከ7 ያላነሰ አስከሬን መገኘቱ ታወቀ
(ኢሳት ዜና ሚያዝያ 05 ቀን 2010 ዓ/ም) የአካባቢው ነዋሪዎ እንደገለጹት ባለፈው ቅዳሜ በጅግጅጋ ቀበሌ 10፣ 17 እና 18 የተፈጠረውን ጎርፍ ተከትሎ በርካታ ዜጎች በጎርፍ ተወስደው ህይወታቸው ያለፈ ሲሆን፣ ኢሳት ዘገባውን ባቀረበ ማግስት የክልሉ ፖሊስ እና መከላከያ ፍለጋ ጀምረው እስካሁን የ7 ሰዎች አስክሬን ተገኝቷል።
የበርካታ ዜጎች አስከሬን አሁንም ድረስ አለመገኘቱን፣ በጎርፍ ከተወሰዱት መካከል የንግድ ባንክ ስራ አስኪያጅ የሆነ ግለሰብም እንደሚገኝበት የክልሉ ዘጋቢያችን ገልጿል።
በጎርፉ አንድ የመብራት ሃይል መኪን ጨምሮ 4 አይሱዙ መኪኖች በጎርፍ ተወስደዋል። አንድ ኮካ ኮላ የጫነ መኪና እስከሙሉ ጭነቱ የተገለበጠ ሲሆን፣ የጫነው ኮካ ኮላም በጎርፍ ተወስዷል። በመኪኖች ላይ የነበሩ ሰዎችም በጎርፍ ተወስደዋል። ጎርፉ በምስራቅ ሃረርጌ ዞን ጭናክሰን ከተማ በዘነበው ዝናብ ምክንያት የተፈጠረ ነው::