በሶማሊያ በደረሰ የቦንብ ጥቃት 14 ሰዎች ሞቱ

(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 14/2010)በሶማሊያ መዲና ሞቃዲሾ በአንድ ሆቴል ላይ በደረሰ የቦንብ ጥቃት 14 ሰዎች ሞቱ።

ፋይል

በመኪና ለይ ተጠምዶ ነበር በተባለው በዚህ የቦምብ ጥቃት በመዝናናት የነበሩ 6 ሰዎች ወዲያውኑ ሲሞቱ ሌሎች ተጨማሪ 8 ሰዎችም በአደጋው ሕይወታቸው ማለፉ ታውቋል።

እንደ ቢቢሲ ዘገባ ከሆነም የሟቾች ቁጥር ከዚህም በላይ ሊጨምር ይችላል። 

ለተፈጸመው የቦምብ ጥቃትም አልሻባብ ሀላፊነት መውሰዱን ዘገባው ጨምሮ ገልጿል።

ባለመረጋጋት ውስጥ በቆየችው ሶማሊያ በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ተደጋጋሚ የአጥፍቶ መጥፋት ጥቃቶች በመድረስ ላይ መሆናቸውን ዘገባዎች አመልክተዋል።